






ባለፉት አምስት አመታት በፓርቲው መሪነት በከተማዋ የተሰሩ ጠንካራ ስራዎችን ለማስቀጠል እንዲሁም 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ እንዲሆን የሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የውይይት መድረክ በማሻ ከተማ ተካሂደዋል ።
በውይይት መድረኩ ላይ መነሻ ሰነድ ያቀረቡት የማሻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አንዷለም ጌታቸው በከተማዋ ባለፋት የአምስት አመታት በርካታ የልማት ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀው በዚህም የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን እንዲሁም የሆስፒታል ግንባታ ተጠናቀው አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑ አንዱ የፓርቲ ትሩፋት እንደሆነ ጠቁመዋል ።
ከዚህ በተጨማሪ በከተማዋ የተጀመሩ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ እንዲሁም የመንገድ መሰረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው አሁንም ፓርቲው በቆራጥነት ይህን ከዳር ለማድረስ እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል ።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በቀረበውን መነሻ ሰነድ በሰጡት አስተያየት ለዘመናት የህዝብ ጥያቄ የነበረው የሆስፒታልና መብራት ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱ፣ የሚዲያ ተደራሽነት መረጋገጡ እንዲሁም የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ መጀመሩ በብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው ውጤት ነው ብለዋል።
የጎሬ፣ማሻ ቴፒ ኮንክሪት አስፓልት መንገድ ግንባታ መጀመሩ ተስፋ የሰጠ ቢሆንም ይህን ከዳር ማድረስ ላይ ልሰራ እንደሚገባ የገለፁት የመድረኩ ተሳታፊዎች ፓርቲው የጀመረውን የልማት ስራ የመጨረስ ባህል ያለው በመሆኑ ትኩረት ማድረግ አለበት ብለዋል።
ቀጣይ በስራ እድል ፈጠራ እና በትምህርት ዘርፍ እንዲሁም ወሰን ማስከበርና ሰላም ማረጋገጥ ላይ ፓርቲው ትኩረት መስጠት እንዳለበትም ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።
ከብልፅግና በፊት በነበረው ስርዓት ፍትሐዊ የልማት ተጠቃሚነት ያልተረጋገጠበት ቢሆንም አሁን ላይ በፓርቲው መሪነት በከተማዋ የተጀመረውን የልማት ስራዎችን ለማጠናከር የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የህዝብ ተወካዮች በበኩላቸው ባለፉት ጊዜያት በተሰራው ስራ በልማት፣በፖለቲካና በሰላም ግንባታ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ እንደተቻለ ጠቁመው ይህን ለማጠናከር ፓርቲው አሁንም በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።
በክልልም ሆነ በሀገር ደረጃ ተስፋ ሰጪ የልማት ስራዎች እየተሰሩ መቆየታቸውን የገለፁት ተወካዮች አሁንም ጠንካራ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን በማስቀጠል ድክመቶችን በማረም እንዲሁም የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማጠናቀቅ ፓርቲው ለህዝቡ ተጠቃሚነት በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል ።
7ተኛው ጠቅላላ ሃገራዊ ምርጫ ነፃ፣ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የበኩላቸውን እንዲወጡ አቅጣጫ የሰጡት ተወካዮች ለወከሉት ህዝብ ተጠቃሚነት አሁንም ተግተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋም ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አዝመራ አንደሞ፣የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የማህበራዊ ክላስተር ዘርፍ አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ፣የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ የሺዋስ አለሙ እና ከሁሉም ማህበራዊ መሰረት የተወጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ሲል ማሻ ኤፍ ኤም ዘግቧል።
