የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል፦የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት

Spread the love

የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጹ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሚዛን አማን ከተማ የተለዬዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ በቤንች ሸኮ ዞን የህዝብን ሁሉአቀፍ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ምልከታ አድርገዋል።

የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ፣የደቡብ ምዕራብ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣የኮሪደር ልማት የስራ እንቅስቃሴውን ተዘዋውረው ተመልክዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በሰጡት አስተያየትም የአውሮፕላን ማረፊያው ሲጠናቀቅ የአካባቢውን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ከማሳለጥ በሻገር ለአካባቢው ወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል

በጉብኝቱ ላይ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ከሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎችና የጋራ ምክር ቤቱ አባላቶች ተሳታፊዎች ሆነዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *