




የክልሉ ህብረት ስራ ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ቀበሌ መንገሻ ኮንፍረንሱን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት ባለፉት 6 አመታት ብልጽግና የሀገሪቱን የማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስብራቶችን በመጠገንና ወደ ተሟላ የብልጽግና ጉዞ እየተጓዘ ይገኛል ብለዋል።
ብልጽግና በሀሳብ ልዕልና የሚያምን እና እንደ ሀገር ከነበርንበት ስጋት በማውጣት ወደ ሚታይና ሚጨበጥ እመርታ ያሸጋገረ ፓርቲ ነው ብለዋል። ባለፉት አመታት በበጋ መስኖ ፣ በሌማት ትሩፋት ፣ በአረንጓዴ አሻራ ፣ በበጎ ፍቃድ ስራዎች ፣ በኢንዱስትሪና ቴክኖሎጂ ዘርፍ እመርታዎች ተመዝግበዋል ብለዋል። ይህን ተግባር ባህልና ዘላቂ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመን ምክትል የቢሮ ኃላፊና የሚዛን ክላስተር መሰረታዊ ድርጅት አመራር አቶ አምዴ ፋሪስ የመወያያ ሰነድ ሲያቀርቡ እንደተናገሩት ለውጥ ተፈጥሯዊና የማይቀር ሂደት መሆኑን ገልጸው ከለውጡ ባህል ጋር አብሮ መዘመን እና ራስን ማዘጋጀት ያስፈልጋል።
መደመር ትላንት ፣ ዛሬና ነገን አስታርቆ የሚጓዝ አስተሳሰብ መሆኑን ገልጸው መደመር የኢትዮጵያን ህልም በእውን እያረጋገጠ ነው ብለዋል። እንደ ሀገር የማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ባህልን ማዘመንና ስብራቶችን በመጠገን ወደ አዲስ ባህልና ሁለንተናዊ ብልጽግና ማሻገር ነው ብለዋል።
ብልጽግና ሰብአዊ ልዕልናን ማረጋጥ ፣ ኢኮኖሚያዊ ሉአላዊነትና አፍሪካዊት ሀያል ሀገር መገንባትን ቁልፍ ተግባር አድርጎ እየሰራበት ይገኛል ብለዋል። አለም ቀጣይነት ባለው የለውጥ ሂደት ናት ያሉት ኃላፊው ሀገራችንም አዲስ የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ልምምድና ትግበራ ውስጥ ትገኛለች ብለዋል።
ለውጡ ስኬታማ መሆን የሚችለውም ሀሳብን ወደ ተግባር መቀየር የሚችል የአስተሳሰብና የአመለካከት ለውጥ ሲኖር ነው ብለዋል። ገዥ ትርክትን ለማፅናት ሀገራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የገለጹት አቶ አምዴ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል።
መድረኩ ቀጥሎ እየተካሄደ ሲሆን አቶ አምዴ ፋሪስ ለምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች ለውይይት መነሻ ሰነድ እያቀረቡ ይገኛሉ።
