




በብልፅግና ፓርቲ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቅ /ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ጋር በመሆን ያለፉትን ዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገምገማ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
በብልፅግና ፓርቲ የክልሉ ቅ /ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ በላይ ተሰማ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት፥ ጠንካራ ፓርቲ የሚገነባው አባላት በጠንካራ አደረጃጀት ሲታቀፉ መሆኑን በመግለጽ፥ ጠንካራ የፓርቲ አደረጃጀት በመትከል ተግባራት በውጤታማነት መምራት ይገባል ብለዋል።
መድረኩ ያለፉትን ዘጠኝ ወራት አፈፃፀሞች ከዕቅድና ከግቦች አንፃር በጥልቀት በመገምገም ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና ጉድለቶችን ፈጥኖ ለማረም የሚያስችል እንደሆነ ያመላከቱት አቶ በላይ የግምገማ መድረኩ በመዋቅሮች መካከል ተሞክሮ እንዲያገኝ በማድረግ ተቀራራቢ አፈፃፀም ለማስመዝገብም የሚያግዝ እንደሆነም አስረድተዋል።
የተደራጀና ጥራት ያለው የአባላት መረጃ አያያዝን በየጊዜው ማዘመን እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ በላይ ተግባራዊ የተደረገው አዲሱ የአደረጃጀት መመሪያም ለፓርቲው አደረጃጀት ተጨማሪ አቅም የፈጠረ እንደሆነ ገልጸዋል።
ጥራት ያለው አባል ማፍራትና ጥራት ያለው መረጃ በመያዝ የፓርቲውን ተልዕኮ እና ዕቅድ በአንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት አሰራርን በየደረጃው ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባም ነው አቶ በላይ ያስገነዘቡት።
የአባላትን አስተሳሰብ በተግባር ተልዕኮ መገንባትን ለማጠናከር የተጀማመሩ ጥረቶች ሊጎለብቱ ይገባል ያሉት አቶ በላይ በመንግሥት የወረዱ ኢንሼቲቮችን በጠንካራ አደረጃጀት መምራት ውጤታማነታቸውን ከህዝብ ተጠቃሚነት አኳያ ማረጋገጥ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በመድረኩ ከክልሉ ሁሉም ዞን የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊዎች እንዲሁም የክልል ማዕከል የብልጽግና ኀብረት አመራሮች የተገኙት ሲሆን፥ በክልል የሁሉም ክላስተር የብልጽግና ቤተሰብ ሪፖርት እንደሚቀርብም ተገልጿል።
በአፈጻጸም ግምገማ መድረኩ የዞኖች ያለፉት ዘጠኝ ወራት የአደረጃጀት ዘርፍ የተግባር አፈፃፀም ሪፖርታቸውን እያቀረቡ የሚገኝ ሲሆን በቀረበው የአፈጻጸም ሪፖርት መነሻ ውይይት ተደርገው በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የተቀናጀ ርብርብ ለማድረግ ተግባቦት እንደሚፈጠርም ተገልጿል።
በዕድገቱ በዛብህ
