ባለፉት 9 ወራት 35 ሺህ 762 ቶን ቡና ወደ ማዕከላዊ ገበያ ቀርቧል:- የቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ባለስልጣን

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ቡና፣ሻይና ቅመማቅመም ባለስልጣን ቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ከምርት ዝግጅት እስከ አቅርቦት ድረስ ላለው ሂደት ልዩ ትኩረት በመስጠት በመጠን እና በጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ደርሶ የተፈለገውን ሀገር ውስጥ ፍጆታና የውጭ ምንዛሬ እንዲያስገኝ እየሠራ እንዳለ ገልጿል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አስራት መኩሪያ እንደተናገሩት የአካባቢውን ምቹ ምህዳር በመጠቀም በቡና ማሳ ሽፋን፣ በቡና ምርት ዕድገት ላይ የሚታዩ ማነቆዎችን በመፍታት እና በምርት ጥራትና አቅርቦት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየሠራ ነው ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ የቡና ሽፋንን ለማሳደግ 46 ሺህ 872 ኪሎ ግራም ቡና ዘር በማዘጋጀት 11 ሺህ 061 ኪሎግራም በክልሉ ማፍሰስ የተቻለ መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ ቀሪውን ዘር ለሌሎች ክልሎች ማስተላለፍ ተችሏል ብለዋል።

ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የፈሰሰዉን ቡና ዘር 72 ነጥብ 3 ሚሊየን የቡና ችግኝ በመለየት የእንክብካቤ ስራ እየተሠራ መሆኑን አቶ አስራት ገልጸዋል።

ከቅመማቅመም ምርት አኳያም 41 ሺህ 197 ቶን ቅመማ ቅመም ለገበያ መቅረቡን የገለፁት አቶ አስራት 3 ሺህ 984 ቶን የሻይ ምርትም ለሀገር ውስጥና ውጭ ገበያ መቅረቡን ተናግረዋል።

በአሻግሬ ገ/ወልድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *