ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በብልፅግና ፓርቲ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤት ከቀረቡ ዕጩዎች ጋር ምክክር እየተካሄደ ነው

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤት በብልፅግና ፓርቲ የቀረቡ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ጋር በቀጣይ ተልዕኮዎች ዙሪያ በቦንጋ ከተማ ምክክር እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣ የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማንና ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲውና የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ብልፅግና ፓርቲ በዘንድሮው 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የፓርቲውን የምርጫ ምልክት ”የስንዴ ነዶ” በማድረግ ለምርጫ ይዘው የቀረበ ሲሆን ምርጫውን በአሸናፊነት በማጠናቀቅ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” ለማሸጋገር ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *