በአንድራቻ ወረዳ የጌጫ ከተማ የህዝብ መድኃኒት ቤት ተመርቆ ለአገልግሎት ብቁ ሆኗል።

Spread the love

የህዝብ መድኃኒት ቤቱን የክልሉ ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ መርቀዋል።

በምረቃው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ወሰን ጨመሰ መድኃኒት በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ የሚቀርብበት ነው ብለዋል።

በመንግሥት ተቋማት የማይገኙ መድኃኒቶች በአማራጭነት ቀርበው ህብረተሰቡ እንዲጠቀም ያግዛልም ብለዋል።

ለአገልግሎት በበቃው የህዝብ መድኃኒት ቤት የሰው ሀይል ቅጥር ለማሟላት ትኩረት ተደርጎ ይሰራል ብለዋል።

የዞኑና የወረዳው መንግስት ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት የተከፈተ ሲሆን ለ24 ሰዓት አገልግሎት እንደሚሰጥም ተጠቅሷል።

በሂደትም ህዝቡ የሚጠይቀውን የጤና ልማት ስራዎችን የክልሉ መንግስት ደረጃ በደረጃ እየመለሰ ይሄዳልም ብለዋል።

ለመድኃኒት ቤት ግዢና ለሌሎች ተግባራት ከወረዳው አስተዳደር 5 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉን የአንድራቻ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አየለ አገሎ ተናግረዋል ።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *