ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ኤምባሲ የልዑካን ቡድን ጋር መከሩ ።

Spread the love

የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ መልዕክተኞች በሁለቱ ወዳጅ ሀገራት ድንበር አከባቢ የሚፈጠሩ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት ቀጠናዊ ትስስርን ለማጠናከር ያለመ ምክክር በቦንጋ ከተማ አካሂዷል።

በሁለቱ ወዳጅ ሀገራት መካከል የቆየውን ታሪካዊ ወዳጅነት በማስቀጠል የህዝብ ለህዝብ ግኑኝነት እና ማህበራዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ትስስር በማስቀጠል እንዳለበት በውይይቱ ተመላክቷል።

ክልሉ ከደቡብ ሱዳን ሪፑብሊክ ጋር ሰፊ ድንበር የሚጋራ በመኾኑ፥ በድንበር አከባቢ የሚከሰቱ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት ቀጣይነት ያለውን ሠላም ማረጋገጥ እንደሚገባ ነው የተገለጸው።

አልፎ አልፎ በድንበር አከባቢ በታጣቂዎች

የሚፈጠሩ ወንጀሎች መኖራቸውንና ከዚህ ወንጀል ጋር በተያያዘ በክልሉ በህግ ጥላ ስር ያዋሉ ተጠራጣሪዎች በመኖራቸው በቀጣይ በሚለቀቁበት ሂዴት ላይ በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

በድንበር አከባቢ የሚስተዋለውን የግጭት አዙሪት በዘላቂነት በመፍታት አውንታዊ ሠላምን በቀጠናው ለማረጋገጥ በሁለቱ ሀገራት ደረጃ እና ድንበር በሚጋራው ክልል መካከል በትብብር ለመስራትም መግባባት ተፈጥሯል።

የድንበር ቀጠና ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት ሠላማዊ ትስስርንና የሁለትዮሽ ግኑኝነትን ለማስቀጠል የደቡብ ሱዳን መንግሥት ቁርጠኛ መኾኑ የገለጹት የልዑካን ቡድኑ አባላት ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን እውነተኛ ወዳጅ ሀገር መኾኑዎን ተናግሯል።

የድንበር አከባቢ ነዋሪዎችን ኑሮ በዘላቂነት በማሻሻል ሠላማዊ የህዝብ ለህዝብ ትስስር መፈጠር አስፈላጊ በመኾኑ ቀጣይ በሁለቱ ሀገራት እና በኢጋድ ደረጃ ውይይት በማድረግ የመሠረተ ልማት ተደራሽነት ማስፋት እንደሚገባም በውይይቱ ተነስቷል።

በውይይቱ፥ በአፍሪካ ህብረት ምክትል ቋሚ ኮሚቴ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴንግ ኦቤድ፣በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ ካውንስለር ሪያክ፣ምክትል ወታደራዊ አታሼ ሜጀር ኦፑል ቻም፣ የኢሚግሬሽን አታሼ አንቲፓሰ ኮሮም ማናር እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *