




በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኤስ ኤን ቪ ፕሮጀክት የአርሶ አደር ማሣ ላይ ት/ቤት (FFS)ተቋማዊ ለማድረግ ያለመ የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ አካሂዷል ፡፡
በመድረኩ በኢትዮጵያ እና በደቡብ ምዕራብ ክልል ምን ምን ስራዎችን እንደሚሰራ በኢትዮጵያ የሆር ላይፍ ፕሮጀክት ማነጀር በሜኑ ኪዘር እና በደቡብ ምዕራብ አካባቢ ስራ አስኪያጅ ወ/ሪት ዓለም ፀሀይ ገነት ስለፕሮጀክቱ አጠቃላይ ገለፃ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና ግብርና ቢሮ ኃላፊ አማካሪና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንሰ መላኩ ፕሮጀክቱ ከክልላችን እምቅ አቅምና ካለው ስህነ ምዳር ምቹነት ፕሮጀክቱ አርሶ አደር ማሣ ላይ ትምህርት ቤት በመክፈት በርካታ ውጤታማ ተግባር እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዛሬ በሚደረገው መድረክ ተጨማሪ ሁለት ወረዳዎች ወደ ፕሮጀክቱ የታቀፉ መሆናቸውን በማብሰር አጠቃላይ የወረዳዎች ብዛት ወደ 11 ከፍ አድርጎ የሚሰራ እንደሚሆንም አብራርተዋል፡፡
አቶ ዮሐንሰን አክለውም ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ መንግሥት ድጋፍና በፕሮጀክቱ የጋራ ትብብር 7 ወረዳዎች በፕሮጀክቱ እንዲካተቱ መወሰኑንና አጠቃላይ የወረዳዎች ብዛት በቀጣይ ወደ 18 የሚደርሱ መሆናቸውን ገልፀዋል ፡፡
ከዚህ በፍት በክልሉ በኤፍ ቲ ስ ከሚንሰራው በላይ ይህን ስራ በአጭር ጊዜ በመስፋት ውጤታማ መሆኑን ጠቁመው የክልሉ መንግሥት የድርሻቸውን ወስዶ የህብረተሰብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቱ 15 አርሶ አደሮችን በቡድን በማደራጀት አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ የተጀመረውን እምቅ አቅም ወደ ፍት አውጥን እንዲንጠቀሚና ተጠቀሚነታችንን ለማረጋገጥ ያሉብንን ክፍታቶችን በማሙላት
ጥናትና ምርምር ስራዎች እየሰራ በመሆኑና በዚህም የቴክኖሎጂ ሽግግሩን በማስፋት አርሶአደሮች በልማቱ ተጠቃሚ የሚሆኑበት አቅጣጫ መከተል አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
ለዚህም ባለድርሻ አካላት ስራው ውጤታማ እንዲሆን የዲርሻቸውን እንዲወጡ አቶ ዮሐንሰን መላኩ አሳስበዋል፡፡
ኤስ ኤን ቪ ፕሮጀክት የደቡብ ምዕራብ አካባቢ ስራ አስኪያጅ ወ/ሪት ዓለምፀሀይ ገነት በበኩሏ የመድረኩ ዋና ዓላማ የአርሶ አደር ማሣ ላይ ት/ቤት (FFS)ተቋማዊ ለማድረግ ያለመ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በ9 ወረዳ ላይ የአርሶ አደር ት/ቤት ተግባራዊ ከማድረግ በተጨማሪ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የተለያዩ ተግባራትን ስሰራ መቆየቱን ተናግራለች ፡፡
ከዚህ በኃላ ስለ ፕሮጀክቱ መንግሥት ኃላፊነት የሚወስድና አጠቃላይ በፕሮጀክቱ የሚሰሩ ስራዎች ከክልሉ መንግሥት ጋር በጋራ በትብብር የሚሰሩ መሆኑን ጠቁማለች፡፡
የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ባለሙያ አቶ አይንሁነኝ መኳንንት በበኩሉ የፕሮጀክቱ ቀጣይነት የመንግሥት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሶ ውጤታማ ለማድረግ መንግሥት እና ፕሮጀክቱ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግም ተናግሯል፡፡
በመጨረሻም በፕሮጀክቱ ለታቀፉ ወረዳዎች ለስራው አጋዥ የሚሆን የሞተር ሳይክል ድጋፍ በማድረግ መድረኩ ተጠናቋል ፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
