



የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2016 ዓ.ም የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ከዘርፉ አመራሮች ጋር አካሂዷል።
በግምገማው መድረኩ ላይ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ማሞ እንደገለጹት መድረኩ የነበሩ ጥንካሬዎች የሚፈተሹበት ፣ዕጥረቶችን ነቅሶ በማውጣት ለቀጣይ ስኬቶች የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
የማህበራዊ ፣የኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ተግባራት አበረታች ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል።
በየደረጃው ያሉ መዋቅሮች ጠንካራ አደረጃጀቶችን መገንባት ላይ በቀጣይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚገባ የገለጹት አቶ ፀጋዬ አደረጃጀቶችን በመፈተሽ ፓርቲው ባስቀመጠው አሰራር መሰረት ከአደረጃጀት እስከ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ በማጤን የመደገፍና የማብቃት ስራን ተቋማዊ አድርጎ ማስቀጠል የቀጣይ ጊዜያት የትኩረት አካል መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል።
በቀጣይ የአቅም ግንባታ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ በማስቀጠል በእውቀትና በአመለካከት የጠራ እንዲሁም በፓርቲው እሳቤ የተቃኘ አባል መፍጠር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች እየተሰሩ ያሉት ስራዎች አበረታች በመሆናቸው ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ አቶ ፀጋዬ አስገንዝበዋል ።
የንቅናቄ ስራዎችን በተደራጀ መንገድ አጠናክሮ በማስቀጠል የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳድር ማነቆዎችን በዘላቂነትና ቀጣይነት መልኩ ርብርብ እንደሚደረገ የገለጹት አቶ ፀጋዬ ለተግባራዊነቱ አመራሩ ህብረተሰቡን በማስተባበር የመሪነት ሚናውን መወጣት እንዳለበት ገልጸዋል።
የወጣቶችና የሴቶችን የስብዕና ግንባታና አደረጃጀት የማጠናከር ስራ ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት ተድርጎ በአጽንኦት መስራት ይገባል ያሉት የፓርቲው የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ተሰማ ናቸው።
የፓርቲያችን ልዩ መገለጫ የበጎነት እሳቤዎች የሆነው ሰው ተኮር ተግባራት በክረምት ወራት ተጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል።
የፓርቲው የፖለተካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ በንቅናቄ አጀንዳ የሚመሩት ተቋማት በቅንጅት እና በትብብር በመስራት የብልጽግና እሳቤዎችን ከዳር ማድረስ አለብን ብለዋል።
በፋይናንስ ዘርፍ ሀብት የማሰባሰብ ተግባር በግልጸኝነትና ተጠያቂነትነን የተላበሰ የአሰራር ስርዓትን መትከል መመራት እንዳለበት ጠቅሰዋል።
በአጠቃላይ በየዘርፉ የተመዘገቡ ውጤቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉ የመጡ መሆናቸው በዝርዝር የተገመገመ ሲሆን በመድረኩ በክፍተት በተገመገሙ ጉዳዮች የቀጣይ ዕቅድ አካል በመሆን በልዩ ትኩረት መመራት እንዳለባቸው ተግባቦት ተፈጥሮል።
