

ርዕሰ መስተዳድሩ በዞኑ እየተከናወነ ባለውና በቀጣይ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ነው ውይይት ያደረጉ።
መንግስት ከሚሰራው የልማት ስራዎች ጎን ለጎን መላው የዞኑን ህዝብ በማስተባበር የዞኑን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ልሰራ እንደሚገባም አንስተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም ባለሀብቶችን በማስተባበርና ኢንቨስትመንትን በመጋበዝ ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር ትልቁ ተግባር ልሆን ይገባልም ብለዋል።
በዞኑ ባለፉት አራትና አምስት የለውጥ አመታት በዞኑ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች አበረታች እንደሆኑ የገለፁ ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የዞኑ ሁለንተናዊ ብልፅግና እንዲረጋገጥ መደማመጥና መተጋገዝ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።
የህብረተሰብ ተሳትፎ ለልማት ሁሉ መሠረት እንደሆነ ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ በዞኑ ተጀምሮ የቆሙ እንደ ባህል አዳራሽ ያሉ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ ሁሉም የዞኑ የተቀናጀ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
የተረጋጋ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ሁኔታ መፍጠር ለአንድ አከባቢ ዘላቂ ልማትና ሰላም ወሳኝ ስለሆነ የዞኑ ህዝብ አንድነቱንና የልማት ትብብሩን አጠናክሮ ልቀጥል እንደሚገባም አስረድተዋል።
በውይይት መድረኩ የተሳተፉ የማህበረሰብ ተወካዮች ለዞኑ ልማትና ለውጥ የሚጠበቅባቸውን ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።


በመድረኩ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የወጣቶችና የሴቶች ተወካዮች፣ የዞን፣የወረዳና ከተና አስተዳደር የስራ ሀላፊዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
