
ባለፉት ስድስት ወራት ከ1 ሚሊየን በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ጠቅላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የሥራ ዕድል ፈጠራን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ በየዓመቱ ከፍተኛ የሆነ የሥራ ፍላጎት መኖሩን ገልፀዋል።
በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ከ1 ሚሊየን በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ጠቁመዋል።
150 ሺህ የሚሆኑ ዜጎችም በውጭ አገራት የሥራ ስምሪት ማድረጋቸውንም ተናግረዋል።
በዚህም በተለያዩ አገራት ስምሪት ያደረጉ ዜጎች መብታቸውና ክብራቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ ጠንካራ ሥራ መሠራቱን አስረድተዋል።
አሁንም በየዓመቱ ካለው ፍላጎት አንጻር ብዙ ጥረት ማድረግ እንደሚጠይቅ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት።
