በካፋ ዞን ሳይለም ወረዳ እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ የልማት ሥራዎች በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በተመራው የዞን ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ እየጎበኙ ነዉ።

Spread the love

በወረዳ ከኤምርኪ አጋሮ ቀበሌ ጀምሮ የተለያዩ የመንገድ መሠረተ ልማቶችና የግብርና ልማት ተግባራት በካፋ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተጎብኝቷል።

ከኤምርኪ ወደ አጋሮ ቀበሌ የሚያደርስ በህዝብ ተሳትፎ እየተሰራ የሚገኝ የአፈር ሥራ ያለቀለት የ7 ኪ/ሜ መንገድ ከፈታ ሥራ የጉብኝቱ አካል ሆኗል።

በተጨማሪ በቴክኖሎጂ ተጠቅሞ ያመረቱት የአርሶ አደር ስንዴ ማሳ እንድሁም የኤምርኪ አርሶ አደር ማሰልጠኛ ውስጥ የሚከናወኑ የተለያዩ የግብርና ውጤቶች ከተጎበኙት ተግባራት መካከል ናቸው።

የኤምርኪ ቀበሌ የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ግርማ ለገሰ ለጎብኚዎች በሰጡት ሙያዊ ገለፃ በኖራ ህክምናና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ለአርሶ አደሮች ሥልጠና በመስጠት ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል።

እንደ ጽ/ቤቱ ኃላፊ ማብራሪያ ስልጠና የተሰጣቸው አርሶ አደሮች ማሣና በአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ የተጎዳውን አፈር በኖራ በማከምና ዘመናዊ ተክኖሎጂ በመጠቀም የተዘራውን ከ1 ሄ/ር በላይ የበጋ ስንዴን ጨምሮ በቀበሌው የተለያዩ የግብርና ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀው በዚህም በቀበሌው በግብርና መስክ ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን አብራርቷል።

ጉብኝት ያደረጉት የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች በወረዳውና በቀበሌዎች በተመለከቱት ነገር ደስተኞች መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይ መስተካከልና ትኩረት መሰጠት አለባቸው ያሏቸውን ገዳዮች ጠቁመዋል።

በመስክ ምልከታዉ የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ፣የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አጥናፉ ኃይሌ፤ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ደመላሽ ንጉሤ፤ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ የመንግስት ረዳት ተጠሪዎች አቶ ታከለ ታምሩና ወ/ሮ ጽዮን ታዬ እንድሁም ሌሎች የዞንና የሣይለም ወረዳ አመራሮች ተሳትፈዋል ሲል የዘገባው የካፋ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *