




“የድህረ እውነት ዘመንን በእውነትና በእውቀት” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አመራሮች፣ ለህዝብ ግንኙነትና ሚድያ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በቦንጋ ከተማ መሠጠቱን ቀጥሏል።
ስልጠናው የድህረ እውነት ዘመንን በአግባቡ ለመረዳት የሚያስችል በቂ ግንዛቤ የተጨበጠበት እና በሚድያ ዘርፍ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለቀጣዩ በማረም እንዴት ማህበራዊ ሚድያን ለ ገንቢ ዓላማ መጠቀም እንዳለበት የሚረዳ ነው።
ከተሳታፊዎች ውስጥ ያነጋገርናቸው የካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ንዑስ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ህብረት ተካ ስልጠናው ከዚህ በፊት ያለን እውቀትና ክህሎት ላይ የተሻለ አቅም ከመገንባቱም በላይ ፓርትያችን ቅቡልነትን አግኝቶ ሁለንተናዊ ብልፅግና እንድያረጋግጥ እንደ ዘርፉ አመራር በእውነትና እውቀት እንዲሁም በጠራ አመለካከት ሞጋች ኮሚኒኬተር እንዲሆን አግዞናል ብለዋል።
ወ/ሮ ህብረት አክለውም ቀደም ሲል በሚድያ አጠቃቀማችን ላይ የነበረውን ክፍተቶች የሚያርም ስለሆነ ስልጠናው የማህበራዊ ሚድያ ጉዳትና ጥቅሞችን ለይተን በማወቅ ህበረተሰችንን በተሻለ ግንኙት መስመር እንድናገለግል የሚያደርግ በመሆኑ መሰል ስጠናዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
የዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ንዑስ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብራሐም አባተ በበኩላቸው ስልጠናው በማህበራዊ በሚድያ የሚሰራጩ መረጃዎች እውነትን መሠረት ያደረጉ እንድሆኑ መስራት እና ስሜት ቀስቃሽ ሀሰተኛ መረጃዎችን በፍጥነት አጣርቶ የጋራ ትርክትን በመውሰድ ትክክለኛ መረጃ ለህዝብ ማድረስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በቂ እውቀት ያስታጠቀ ነው ብለዋል።
አቶ አብራሐም አክለው በቀጣይም አሰባሳቢ የሆኑ የሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ስራዎችን በመስራት መንግስት የጀመራቸውን የልማት ስራዎች አጠናክሮ ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረት ላይ የበኩላቸው ኃላፊነት እንደሚወጡ ተናግረዋል።
የምዕራብ ኦሞ ዞን መኤኒት ጎልድያ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ ከድር ይመር በበኩላቸው ዘመኑ የመረጃ ፍጥነት፣ ጥራት እና ተደራሽነት በእጅጉ የተወሳሰበበት በመሆኑ ሁሉም ማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች በብቃት እና በእውቀት መጠቀም እንዳለባቸው ገልፀዋል።
ከሸይ ቤንች ወረዳ የመጡ ወ/ሮ ሂሩት ገብሬ እና ከቴፒ ከተማ አስተዳደር የመጡ ወ/ሮ ሀይማኖት ሁሴን በበኩላቸው ከዚህ ቀደም በማህራዊ ሚድያ የሚሰራጩ መረጃዎችን በጅምላ ሲንወስድ ነበረ ብለው ከዚህ ስልጠና ባገኘነው እውቀት ተነስተን የልማት ስራዎችን ወደፊት የሚያስቀጥሉ ጉዳዮች ላይ በንቃት እንሳተፋለን ብለዋል።
አስተያየት ሰጪዎቹ አክለው አብዛኛው አመራርና አባላት የዲጅታል አመራጭ ተጠቃሚ ስለሆነ ፓርቲው የሚተገብራቸውን ፕሮግራሞችና ኢኒሼቲቮች በራሳቸው ማህበራዊ ሚድያ አማራጮች ለህዝቡ በማሳወቅ የሀሰት ትርክቶችን ማክሰም ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
