




በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የCRFL እና REDD+ ፕሮጀክቶች ውህደት ላይ የባለድርሻ አካላት የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ የCRFL እና REDD+ ፕሮጀክቶች ከዓላማቸው አንፃር ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አርንጓዴ ልማትን እውን ለማድረግ በሚደረገው ርብርብ እንዲሁም በሀገራችን በክቡር ጠቅላይ ሚ/ር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) የተጀመሩ አርንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ከዳር ለማድረስ ያበረከቱት አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የREDD+ ፕሮጀክቶች በክልሉ በ29 ወራዳዎች እንዲሁም የCRFL ፕሮጀክት በካፋ ዞን በ9 ወረዳዎች ደን ጥበቃ ሥራ ባሻገር ደንን ያለአግባብ በመቁረጥ መተዳደሪያቸው ያደረጉ የህብረተሰብ ክፍሎችን በኑሮ ማሻሻል ሥራዎችን እየሠራ መቆየቱን ወ/ሮ ወሰነች ጠቁመዋል፡፡
ወ/ሮ ወሰነች አክለውም እነዚህ ሁለቱ ፕሮጀክቶች ባለፉት በርካታ ዓመታት ለየብቻቸው ሲተገብሩ የቆዩና አሁን ላይ በለጋሽ ሀገራትና በኢትዮጵያ መንግሥት የጋራ ስምምነት ፕሮጀክቶቹ ከሀምሌ 1/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በREDD+ ስር እንዲዋሂዱ ከስምምነት ላይ መድረሱን ገልፀዋል፡፡
የክልሉ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አስራት ገ/ማሪያም በበኩላቸው የክልሉን የተፈጥሮ ፀጋ በአግባቡ በመምራት እና በእውቀት በማስተዳደር የህብረተሰብ ኑሮ ለመቀየር እንደክልል ትልቅ የፖለቲካ ትርጉም ተሰጥቶ እየተመራ መሆኑንና በዚህም ወጤታማ ተግባራት መከናወን መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በዚህም የመንግሥትና የተለያዩ ረጂ ድርጅቶች ሚና የጎላ ነው ያሉት ዶ/ር አስራት በተለይም የተፈጥሮ ሀብቶችን በአግባቡ እንዲንጠቀም በግንባር ቀደምትነት የCRFL እና REDD+ ፕሮጀክቶች በፋይናንስ ዘርፎች ሲደግፉን ቆይተዋል ብለዋል፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
