የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በአድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።
የናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት የኢትዮዽያና ህንድን የቆየ ታሪካዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት የሚያሸጋግር ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የመላ ጥቁር ህዝቦች የነጻነት ተምሳሌት የሆነውን የአድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።
ኢትዮጵያ እና ህንድ በዲፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚ፣ በባህል ግንኙነት የረጅም ጊዜ ታሪክ አላቸው።