በመደመር እሳቤ ተግባራዊ የተደረጉ ስራዎችን ወደ ጠንካራ የፖለቲካ፣የኢኮኖሚ እና ልዩ ልዩ የባህል እሴቶች መቀየር ተገቢ መሆኑ ተገለጸ

Spread the love

በመደመር እሳቤ ተግባራዊ የተደረጉ ስራዎችን ወደ ጠንካራ የፖለቲካ፣የኢኮኖሚ እና ሌሎች የባህል እሴቶች መቀየር ተገቢ ነው ሲሉ አቶ ፋጅዮ ሳፒ ገለጹ።

“ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል በካፋ ዞን የዞን ማዕከል ፣ ወረዳና ከተማ አስተዳደር የአጠቃላይ አመራሮች የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የምክክር ሰነዱን ያቀረቡት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጅዮ ሳፒ በመድረኩ እንደገለፁት በብልፅግና ፓርቲ መሪነት ባለፉት የለውጥ ዓመታት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እሳቤዎች እና ልምምዶችን በተለወጠ እና አዲስ የሆነ የስራ ባህል በመተግበር ተጨባጭ ስኬቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ልዩ ልዩ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱም ገልጸዋል።

ከሳምንታት በፊት በሀገር አቀፍ ደረጃ የብልጽግና ስራ አስፈፃሚና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም እንደ ክልል ያለፉትን ሶስት ተከታታይ ዓመታት ጉዞ እና በአንደኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎች እንዲሁም የሁለተኛው ጉባኤ ዝግጅት ላይ ሰፊ ዉይይት መደረጉን ተናግረዋል።

በዚህም ያለፍንባቸው መንገዶች ያስመዘገብናቸው ውጤቶች እና ያጋጠሙ ችግሮችን በመገምገም ለቀጣይ ውጤት መረባረብ ያስፈልጋል ሲሉ አብራርተዋል።

በስራው ጠንካራ፤ በፖለቲካ አቅሙ የተሻለ የብልጽግናን አስተሳሰብ፣ ባህል፣ እሴት እና መርሆዎች የተላበሰ አመራር መፍጠር ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት አቶ ፋጅዮ ለፓርቲው ጉባኤ የሚሳተፉ አባላትም በዚህ መመዘኛ የሚያልፉ መሆናቸውን አብራርተዋል።

በተጨማሪም ተሻሽሎ የቀረበ የብልጽግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ በካፋ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ አጥናፉ ኃይሌ ቀርቧል።

በመቀጠል የብልጽግና ፓርቲ የኢንስፐክሽንና የስነምግባር ኮሚሽን ሰነድ በዞኑ የስነምግባርና ስነምግባር የኮሚሽን ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ተመስገን ገ/ጊዮርጊስ ቀርቧል።

በቀረቡት ሰነዶች ዙሪያ በአመራሩ በኩል ጥያቄ ሀሳብና አስተያየት ተነስቶ ጠንካራ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩ የዞን ማዕከል የወረዳና የከተማ አስተዳደር አጠቃላይ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ዘገባው ካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *