ስኬታማ ሀገራዊ ለውጥ ለማምጣት በየ ደረጃው ያለ አመራር በቁርጠኝነት መሠራት እንዳለበት ተጠቆመ።

Spread the love

“ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል ለዞን ፣ ለወረዳና ለከተማ አስተዳደር አመራር የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ኢንጂነር በየነ በላቸው በምክክር መድረኩ እንደተናገሩት ለውጥ ተፈጥሯዊና የማይቀር ሂደት መሆኑን ገልጸው ከለውጡ ባህል ጋር አብሮ መዘመን እና የተሳካ የባህል ለውጥ ማምጣት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

መደመር ትላንት ፣ ዛሬና ነገን አስታርቆ የሚጓዝ አስተሳሰብ ሆኖ የኢትዮጵያን ህልም እያረጋገጠ የመጣ መሆኑን አስታውሰው ቀደም ስል እንደሀገር የተለመደው ለውጥ የሀገሪቱን እሴት እና ባህልን ያልጠበቀ ነው ስሉ ኢንጂነር በየነ ገልጸዋል።

ኢንጂነር በየነ አክለውም የመደመር ጉዞ አሁን እንደ ሀገር የተጀመረውን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ባህልን ማዘመንና ስብራቶችን በመጠገን ወደ አዲስ ባህልና ሁለንተናዊ ብልጽግና ማሻገር ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ህልማችን ሰብአዊ ልዕልናን ማረጋጥ ፣ ኢኮኖሚያዊ ሉአላዊነትና አፍሪካዊት ሀያል ሀገር መገንባትን ቁልፍ ተግባር መሆኑን በማስረዳት አሁን ሀገራችን አዲስ የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ልምምድና ትግበራ ውስጥ እንደምትገኝም ገልጸዋል።

አንደኛ ጉባዔ ላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አንዱ ገዥ ትርክትን ለማፅናት ሀገራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የገለፁት ኢንጂነር በየነ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል ስሉም አስረድተዋል።

የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ እጅ ለእጅ በመያያዝ በውጤት የታጀበ ሥራን ለመሥራት በየደረጃው የሚገኙ የመንግሰትና የፓርቲ አመራር ተቀናጅቶ ልሥራ እንደምገባ አሳስበዋል።

በውይይቱ ከ 5 መቶ በላይ የዞን ፣ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *