




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ እርሻና ሆርቲ ካልቸር ልማት ዘርፍ FSRP፣ CALM፣ PACT እና SLMP ፕሮግራም ጋር በመቀናጀት ለዞንና ወረዳ ግብርና ባለሙያዎችና ለችግኝ ጣቢያ አስተባባሪዎች በአቮካዶ ማጋባት/ Grafting/ ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና በቴፒ ከተማ እየሰጡ ይገኛል።
በመድረኩ የተገኙት የቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ደረጀ ቱሉ፤ ማዕከሉ ዘርፈ ብዙ ግብርና ስራዎች ላይ ችግር ፈቺ የሆኑ ምርምሮችን በማድረግ ለአርሶ አደሩ ቴክኖሎጂዎችን የማቅረብ ስራ እየሰራ መሆኑን መግለጻቸውን ገልጸዋል፡፡
ማዕከሉ በዋናነት አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂ የመመንጨት፣ ማባዛት እና ለአርሶአደሩ መስጠት እና አጠቃቀሙን በሚመለከት በሣርቶ ማሣያ የማሳየት እና የተለያዩ ስልጠና ድጋፍ መስጠት መሆኑን ተናግረዋል።
በቅመማ ቅመም ዘርፍ ላይ ምርምር ከማድረግ ባሸገር በተለያዩ ሰብሎች፣ በእንስሳትና በፍራፍሬ ምርቶች ላይ ውጤታማና የማህበረሰቡ ፍላጎት መሠረት ያደረጉ በርካታ የምርምር ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ የፍራፍሬ ልማት ባለሙያ አቶ ምትኩ መንገሻ በበኩላቸው ክልሉ በፍራፍሬ ልማት ዘርፍ በኢንሸቲቪ ከሚሰሩ ተግባራት አንዱ የአቮካዶ ተክል ማጋባት/ Grafting/ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ በቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል ላይ ለ3 ተከታታይ ቀናት እየተሰጠ ያለው የአቮካዶ ተክል ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና መሆኑን ጠቁመዋል።
እንደ ክልል በዘንድሮው አመት ክልላዊ ኢንሸቲቪ ዕቅድ መታቀዱንና በ6 ኢንሸቲቮች ላይ መሠረት በማድረግ ለመስራት ሙሉ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ስራ እየተገባ መሆኑንና ከነዚህም አንዱ የአቮካዶ ኢንሸቲቪ ነው ብለዋል፡፡
በክልሉ ከ48 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት አቮካዶ ሽፋን መኖሩንና በየዓመቱ ከ5.5 ሚሊየን በላይ ኩንታል ምርት ይመረታል ያሉት አቶ ምትኩ የሚመረተው የአቮካዶ ምርት ካለው ሽፋንና አንፃር ምርታማነቱ በቂ አለመሆኑንና የተሻሻሉ የአቮካዶ ዝሪያዎች በበቂ ደረጃ ያላመስፋፋት ጉድለት መኖሩን ተናግረዋል፡፡
አቮካዶ ክልላዊ ኢንሸቲቭ አድርጎ መነሳት የዘርፉን ተግዳሮቶች በመለየትና የባለሙያዎችን የክህሎት ክፍታት በስልጠ መሙላት ወሳኝ በመሆኑ ከዛሬ ጀምሮ በቴፒ ግብርና ምርምር ማዕከል ላይ ለ3 ተከታታይ ቀናት የአቮካዶ ተክል ላይ እየተሰጠ ያለው የአሰልጣኞች ስልጠና መሆኑን ጠቁመዋል።
በተከተል ወ/ሚካኤል
