






በጉባኤው ባለፉት 6 ወራት በመደበኛና በማዘጋጃ ከ1 ቢሊዮን 4 መቶ 92 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ገለጹ።
የህዝባችንን የመልካም አስተዳደሪና የልማት ጥያቄዎችን በተገቢው ምላሽ በመስጠት የኢኮኖሚ አቅም ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ተናግረዋል።
በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ግማሽ አመት በመደበኛ እና በማዘጋጃ ገቢ 1 ቢሊዮን 408 ሚሊዮን 491 ሺህ 1 መቶ 97 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 1 ቢሊዮን 492 ሚሊዮን 191 ሺህ 2 መቶ 9 ብር ከ89 ሣንቲም ይህም ከ100% በላይ መሰብሰብ እንደተቻለ አስረድተዋል።
ይህ አፈፃፀም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 7 መቶ 20 ሚሊዮን 6 መቶ 58 ሺህ 5 መቶ 32 ብር ብልጫ ያለበት መሆኑን በሪፖርቱ አመላክተዋል።
የገቢ ሰባሰብ ስራ ውጤታማ ለማድረግ ለሚመለከታቸው አካላት በወቅቱ ዕቅድ በመስጠት፣በየቀኑ እና በየወቅቱ ክትትል በማድረግ፣የቴክኖሎጂ ተደራሽነትን በማረጋገጥ፣የታክስ ማጭበርበርና ስወራን ክትትል በማድረግና መሰል ስራዎች በመስራት ከዕቅድ በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገልጸዋል።
ዘላቂነት ያለውን የገቢ ዕድገት ለማረጋገጥ አዳዲስ ግብር ከፋዮችን በመመዝገብ የግብር ከፋዮችን ቁጥር 19 ሺህ 2 መቶ 65 ለማድረስ እንደተቻለው ተናግረዋል ሲል የዘገበው የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።
