
መንገድ ትራፊክ አደጋ መጠን ለመቀነስና የማሽከርከር ስነ-ባህርይ ላይ በክልላችን ሁሉም ዞኖች የነባር አሽከርካሪዎች ተሃድሶ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት የቢሮ ምክትል ኃላፊና የትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊ ኢንጅነር ዘመዴ አንዳርጌ እንዳሉት በክልሉ ለ19 ሺህ ነባር አሽከርካሪዎች የተሃድሶ ስልጠና በ32 ማዕከላት እየተሰጠ እንደሆነ ገልጸዋል።
ኃላፊው ስገልፁ በግል በማህበራትና በመንግስት ተቋማት ሥር የሚሰሩ የህዝብ የጭነት እና የሞተር ሣይክል ነባር አሽከርካሪዎች በተመቻቹ የማሰልጠኛ ማዕከላት ሥልጠናቸውን እንዲወስዱ በቂ ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ ስልጠና እየተሰጠ ስሆን እስካሁን በኮንታ ዞን ,ምዕራብ ኦሞ ዞንና ሸካ ዞን ከ 3,000 በላይ አሽከርካሪዎች ስልጠና ወልደዋል::
በካፋ, ቤንች ሸኮና ዳውሮ ዞኖች ከጥር 27 ጀምሮ እስከ የካቲት ወር የመጀመሪያ ሣምንት ድረስ በተመረጡ ማዕከላት ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል።
በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ስልጠናውን የወሰዱ አሽከርካሪዎች በክልሉ የተረጋገጠ ሰርትፍኬት የሚሰጣቸው ስሆን ባልሰለጠኑት ላይ ቁጥጥር ተደርጎ በደንብ 557/2016 መሠረት እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል።
ስለዚህ ይህንን በማወቅ በክልላችን የሚገኙ የግል ,የማህበራትና የመንግስት ተቋማት ሥር የሚሰሩ የህዝብ የጭነት እና የሞተር ሣይክል አሽከርካሪዎች በያላችሁበት ዞን በሚወጣው ፕሮግራም መሠረት ስልጠና እንድትወስዱ አሳስበዋል ሲል የዘገበው የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ነው።
