ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የኢቢሲ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ

Spread the love

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር የሆኑትን ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢነት ሹመትን አፀደቀ።

ምክር ቤቱ ለኮርፖሬሽኑ ቦርድ አባልነት የቀረቡ ዘጠኝ ዕጩዎችን ሹመት አፅድቋል።

በዚህም፦

ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት – የቦርዱ ሰብሳቢ (የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር)

ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) – የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር

ዶ/ር መቅደስ ዳባ – የጤና ሚኒስትር

እንደገና አበበ (ዶ/ር) – የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ

አቶ ቸሩጌታ ገነነ – የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ

ጌታቸው ድንቁ (ዶ/ር) – የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር በአዲስ አባልነት ተሾመዋል፡፡

የቀድሞ የቦርድ አባል የነበሩት አቶ ጃፋር በድሩ (የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር)፣ አቶ የሱፍ ኢብራሂም (የአብን ፓርቲ አመራር) እና አብዱልዋሳ አብዱላሂ ( ዶ/ር) (ከብልጽግና ፓርቲ) አባልነታቸው እንዲቀጥል ተደርጓል።

ምክር ቤቱ ከዚህም ባሻገር አቶ ልዑል ካሳዬ ወልዱ እና አቶ ምትኩ ማዳ ድልነሳው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾሟል።

ምክር ቤቱ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመትንም አፅድቋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *