የዲዚ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የምስጋና በአል “ከያ ቢያርግ” መከበሩ ባህላቸውን ወደፊት እንዲወጣ እድል እንደፈጠረላቸው የቤሮ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ

Spread the love

በአሉን የማስተዋወቅ ወደፊት የማውጣት ስራ ተጠናክሮ እንደሚሰራ የቤሮ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አራጋው ይመር አስታውቀዋል።

የዲዚ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በአል “ከያ ቢያርግ” የተጣላ የሚታረቅበት፣ የደረሰ እህል የሚቀመስበት፣ ለቀጣይ አዝመራ የእርሻ መሳሪያዎች ለእርሻ የሚዘጋጁበት በመሆኑ በአሉ በብሔረሰቡ ዘንድ ታላቅ ትርጉም ያለው መሆኑ ተጠቁሟል።

በአሉ በባለፉት ሀምሳ አመታት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን ዘንድሮ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።

የዲዚ ብሔረሰብ አንዱ መገኛ የሆነው በቤሮ ወረዳ በጀባ ከተማ በተከበረበት ወቅት የተገኙት አቶ ይታያል ብረሀኑ እና ወይዘሮ ሩቂያ ዳውድ እንደተናገሩት የበአሉ መከበር የህዝቦችን አንድነት ያጠናከረ፣ ፍቅርን፣ ይቅርታን ያሳዬ ትልቅ በአል መሆኑን ጠቁመዋል።

የበአሉ መከበር የከተማዋን እንቅስቃሴ የሚያሳድግና አከባቢዎቹን ለእንግዶች የሚያስተዋውቅ ትልቅ በአል እንደሆነም ተናግረዋል።

የማጠቃለያ መረሀ ግብሩ በማጂ ወረዳ እንደሚከበር ያሳወቁት ነዋሪዎቹ፥ በበአሉ ላይ በመገኘት በአላቸውን ለአለም እንደሚያስተዋውቁ ጠቁመዋል።

በቀጣይ በአሉ ቀጣይነት ኖሮት ህዝባዊ በአል ሆኖ እንዲከበር የበኩላቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል።

የቤሮ ወረዳ ባህል ቱሪዝም ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ናትናኤል ኢሳያስ በበኩላቸው፥ ለወረዳው ኢኮኖሚ የሚያመነጩ እና ለቱሪዝም መስህብ የሚሆኑ በርካታ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ሀብቶች ቢኖሩም፥ ከዚህ ቀደም ያልተዋወቁ ወደፊት ያልወጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል ።

የዚህ በአል መከበር የብሔረሰቦችን ባህል ወደፊት የማውጣት እድል የፈጠረ የቱሪዝም እንቅስቃሴን የሚያሳልጥ እንደሆነም ተናግረዋል።

የቤሮ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪው አቶ አራጋው ይመር በበኩላቸው በአሉ መከበሩ አብሮነትን ከማስቀጠል ባለፈም በአከባቢው ይታይ የነበረውን የእርስ በእርስ ግጭት ያስቆመበት ይቅርታን ያስተማረ በአል ነው ብለዋል።

በአከባቢው በርካታ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ያለበት ቢሆንም በጥቃቅን ምክንያት በተገቢው መጠቀም ያልተቻለበት ሂደት እንደነበር አስታውሰው፥ የበአሉ መከበር የአከባቢን ጸጋ ለይቶ በተገቢው በጋራ መጠቀም የሚያስችል አቅም መፍጠሩንም ተናግረዋል።

በአሉ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የጎሳ መሪዎች ያሳተፈ መሆኑ ትልቅ ትርጉም ይሰጠዋል ብለዋል።

በቀጣይም በአሉ በአለም ቅርስነት እስኪመዘገብ ድረስ ህዝባዊነትን አጠናክሮ እንደሚሰራም ተናግረዋል።

በአሉ በቀጠይም የማጠቃለያ ስነስረአቱ በማጂ ወረዳ የሚከበር በመሆኑ በዛ ላይም የወረዳው ህዝብ በማሳተፍ በድምቀት እንደሚያከብሩም ጠቁመዋል ሲል ደሬቴ ድ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *