ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ትልቋ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ሳቢ አገር ናት – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Spread the love

ኢትዮጵያ አሁንም በምስራቅ አፍሪካ ትልቋ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ሳቢ አገር ናት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላቀረበላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሸ፤ ሃገሪቱ ከለውጡ በፊት 19 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ስትገኝ እንደነበርና ከለውጥ በኋላ 23 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማመንጨት መቻሉን ተናግረዋል።

በበጀት ዓመቱም 3 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ እንደተቻለ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ስንዴን ጨምሮ በቅባት እህል፣ ወርቅ፣ ጥራጥሬ፣ ቡና እና የአበባ ምርቶች ላይ የተሻለ የወጪ አፈጻጸም መታዩትን ተናግረዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት ከምርትና አገልግሎት ወጪ ንግድ ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኙት እና ከሐዋላ አገልግሎትም 6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ገቢ መገኘቱን ጠቅሰዋል፡፡

ባለፉት 11 ወራት መንግስት 466 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የተቀሱት ጠቅላይ ሚኒሰትሩ፤ ይህም ከተያዘው እቅድ አንጻር የ96 በመቶ አፈጻጸም አለው ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *