ሚዲያው በተደራጀ መንገድ አየር ላይ እንዲወጣ ስራ አመራር ቦርዱ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እያደረገ ይገኛል፦ አቶ ፍቅሬ አማን

Spread the love

‎የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አመራር ቦርድ ውይይት በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

‎በውይይቱ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ፍቅሬ አማን ሚዲያው በተደራጀ መንገድ አየር ላይ እንዲወጣ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

‎አቶ ፍቅሬ አክለውም ክልሉ የሚዲያ ተቋም አስፈላጊነት በመገንዘብ በሰጠው ትኩረት ክልሉ የራሱ ሚዲያ በማደራጀት በዌብሳይትና በማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል።

‎ሚዲያው የህብረተሰቡን የመረጃ ተደራሽነት ከማረጋገጥ ባሻገር የክልሉን እምቅ ፀጋ በመግለጥ ረገድ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ቦርዱ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል ብለዋል።

‎በመድረኩ የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የ2017 ዓ.ም አፈፃፀም በሚዲያ ኔትወርኩ ዋና ስራ አስኪያጅ ቀርቧል።

‎አቶ መንግስቱ ባቀረቡት ሪፖርት ተቋሙ ከተደራጀ ወዲህ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው አሁን ላይ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ስራዎችን ለማስጀመር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

‎እንዲሁም የሚዲያ ተቋሙ የ2018 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ በሚዲያ ኔትወርኩ ምክትል ስራ አስኪያጅና ይዘት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ካሳሁን ወዳጆ ቀርቦ የሚጸድቅ ይሆናል።

‎ስራ አመራር ቦርዱ የተቋሙን የ2017 አፈፃፀምና የ2018 ዕቅድ፤ የቴሌቪዥንና የስቱዲዮ ግንባታ ሂደት፤ የሚዲያውን ኢዲቶሪያል ፖሊስን ጨምሮ የተለያዩ መመሪያዎችን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ደብብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *