




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ምክክር ዙሪያ የሴክተር ጉባኤ መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካኸደ ነው።
መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ የያዝነው በጀት ዓመት ሀገራችን ለዘመናት ከነበረችበት ታሪካዊና ማህበራዊ ኩስምና ተላቃ የመቻል እና የመወሰን አቅማችንን በብዙ ፕሮጀክቶች ያየንበት በመሆኑ የዝህ ዘመን ሴቶች፣ወጣቶች፣ህጻናት፣ አረጋዊያን እና አካል ጉዳተኛች እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።
በክልሉ በ2017 በጀት ዓመት አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸው የጠቁሱት ኃላፈዋ በዘንድሮ በጀት ዓመት መደገም የሌለባቸው ነጥቦች ተለይተው እስትራቴጂያዊ አቅጣጫ እንደተቀመጠ ገልጸዋል።
የአንድ ሀገር ዕድገት የሚረጋገጠው ከመንግስት በሚመደበው በጀት ብቻ ያለመሆኑን ያወሱት ወ/ሮ ገነት: በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሁሉም መዋቅሮቻችን በተደረገው ንቅናቄ ስራው በየዓመቱ መሻሻሎችን ከማሳየቱም ባሻገር አሁን በማህበረሰባችን ውስጥ ባህል ወደ መሆን ላይ ደርሷል ብሏል።
በ2017 ክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሌሎችንም ህብረተሰብ ክፍል በማሳተፍ 1 ሚልዮን 33 ሺ በላይ ዜጎች ተሳትፈውበት አገልግሎት ተሰጥቷል ያሉት ኃላፊዋ በቀሪ ቀናትም የሚቀጥል መሆኑን ጠቁመዋል።
የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ እና ማህበራዊ ፍትህ ለማስፈን የቅድመ አንደኛ ትምህርት ፕሮግራምን ቢሮአችን ይደግፋል ብለው ተተኪ ትውልድ ለማፍራት ሴቶችና አካል ጉዳተኞች በዘርፉ እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከወትሮ የተሻለ ስራ ይጠበቅብናል በለዋል።
የሴቶችና ወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ጠንካራ አመራር ሰጥተን ተጠቃሚነታቸውን እናሳድጋለን ብለው በዝህም የብድር አቅርቦት፣ የቁጠባና የስራ ባህል እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማሳደግ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
የሴቶች ልማት ህብረት ከዝህ ቀደም በተያዘው ፍጠነት አደረጃጀታቸው ሊቀጥል ይገባል ያሉት ወ/ሮ ገነት በተለይ የሴቶች እና ህፀናት ጥቃት ለመከላከል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በንቃት እንዲሳተፍ አስገንዝበዋል።
የገራችን ኢኮኖሚ በፈጠራ እንዲደገፍ የወጣቶች እና ህፃናት ፈጠራ ተግባራት እናጠናክራለን ብለው ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሴቶች፣ህፃናት፣ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች እኩል ተጠቃሚነትን እንዲያስጠብቁ ጥሪ አቅርበው ጉባኤውን አስጀምረዋል።
በጉባኤውም የተለያዩ የክልል እና የዞን አመራሮች፣ የረጋዊያን እና አካል ጉዳተኞች ተወካዮች፣ የወጣቶች ፌደሬሽን ተወካዮች እና የማህበረሰብ ድርጅት ተወካዮች እየተሳፉበት ይገኛል።
በአሻግሬ ገ/ወልድ
