የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ውጤታማ ለመሆን የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት እንደሚገባቸው ተገለፀ

Spread the love

የቤንች ሸኮ ዞን ሥራ ክህሎት ኢንተርፕራይዝ ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ የ2017 የ4 ወራት ተግባር አፈፃፀም ግምገማና የክህሎት መር የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት እንደ ሀገር ከአለንበት ድህነት ሊያወጣ የሚችለውን የክህሎት መር እንዲሆን ፖሊሲና ስትራቴጂ ወጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በክህሎት መር ለወጣቶች ስራ ዕድል በመፍጠር ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር ያሉ ክፍተቶችን ማረም እንደሚገባ ተናግረዋል።

በዞኑ በርካታ የስራ ዕድል የሚፈልጉ ሥራ አጥ ወጣቶች መኖራቸውን አቶ ሀብታሙ ጠቁመው ከዚህ በፊት ለወጣቶች ሥራ ዕድል የተሰራጨ ገንዘብን አስመልሶ መልሶ ለወጣቶች ለስራ ዕድል ፈጠራ ለመጠቀም ተግዳረቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።

ለወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ የተሰራጨ መመለስ ያለበት ገንዘብ በመደበኛ መንገድ በሚገባ ባለመመለሱ ዞኑ ግብረ ሀይል በማቋቋም በ3 ወራት የተሰራ ስራ መኖሩን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

የዞኑ ሥራ ክህሎት ኢንተርፕራይዝ ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል አሰፋ እንደገለፁት የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ካልሰሩ ውጤት ሊመጣ እንደማይችል ተናግረዋል።

በዞኑ ለወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ተሰራጭቶ ያልተመለሰውን ለማስመለስ በዞኑ ልዩ አስመላሽ ግብረ ሀይል በማቋቋም በሦስት ወራት ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ ማስመለስ መቻሉን አቶ ሳሙኤል ጠቅሰዋል።

የ2017 የ4 ወራት ተግባር አፈፃፀም ግምገማና የክህሎት መር የንቅናቄ ሰነድ እየቀረበ ይገኛል።

በንቅናቄው መድረክ የወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎችና ከንቲባዎች ፣የኦሞ ባንክ ስራአስኪያጆች ፣ የዘርፉ የጽ/ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው ሲል የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *