dvfd

Spread the love

‎የክልሉ የፍትህ ቢሮ የ6 ወር ስራ አፈፃፀምና የ5 አመት ስትራቴጂ ዕቅድ ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

‎የምክክር መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ ምክር ቤት አፈ_ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ መንግስት የዜጎችን የፍትህ የማግኘት መብት በአግባቡ ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው ዘርፎች አንዱ መሆኑን ገልፀው በክልሉ የፍትህ ተደራሽነትና ውጤታማነት እያደገ መምጣቱን ገልፀዋል።

‎በክልሉ በተለይ የባህላዊ ፍርድ ቤቶች አደረጃጀት በአዋጅ ፀድቆ ተግባራዊ መሆን መጀመሩ የፍትሐዊነት የተደራሽነት ችግሮችን በእጅጉ መቀነሱን ገልፀዋል።

‎ተቋም ከመትከልና ከቅንጅት ጋር ተያይዞ የሚገጥሙ ውስንነቶች በማረም አሁንም ለፍትህ ተደራሽነትና ውጤታማነት መትጋት ይገባል ብለዋል።

‎የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ቤቴልሄም ዳንኤል በበኩላቸው የክልሉ ፍትህ ቢሮ፤የህግ የበላይነትን ማረጋገጥና የወንጀል ህጎችን ማስከበር ላይ በሰራው ስራ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።

‎በ2018 በስድስት ወራት ውስጥ በሁሉም የወንጀል ምርመራ መዝገቦች የማጣራት ምጣኔ 93.5% ማድረስ እንደተቻለ ገልፀው የማስቀጣት ውሳኔውም ወደ 94% ማድረስ ተችሏል ብለዋል።

‎የወንጀል አቃቤ ህጎችን አቅም ማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው በዚህም በበጀት ዓመቱ ለ275 አቃቤ ህጎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጥቷል ብለዋል።

‎7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ እንዲሆን በየደረጃው ያሉ የፍትህ ተቋማት ሚናቸውን በአግባቡ እንድወጡም ጠይቀዋል።

‎በመድረኩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የፍትህ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

‎በንጉሴ ወልደየስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *