
በቤንች ሸኮ ዞን በተካሄደ የአመራር ምዘናና ግምገማ፣ 134 አመራሮችን ከኃላፊነት የማንሳት፣ የማሸጋሸግና በአዲስ የመመደብ ሥራ መከናወኑን የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደግፌ ኩድን አስታወቁ።
እንደ ኃላፊው ገለጻ፣ ምዘናው የ2017 ዓ.ም. አፈጻጸምን መሠረት በማድረግ የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን የሚመልስ ብቁና ጠንካራ አመራር ለመፍጠር ያለመ ነው።
በዚህም መሰረት፡-
42 አመራሮች ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል፤
56 አመራሮች እንዲሸጋሸጉ ተደርጓል፤
36 አዳዲስ አመራሮች ወደ ኃላፊነት መጥተዋል።
አቶ ደግፌ አዲስ የተመደቡት አመራሮች የተጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጡ ማሳሰባቸውን የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
