



የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የጣቢያው የበላይ ጠባቂ አቶ ፍቅሬ አማን የቤንች ሸኮ ቴሌቪዥን ጣቢያን አደረጃጀት ጎብኝተዋል።
ኃላፊው የጣቢያው ዝግጅት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው፣ ፈጥኖ ወደ ስርጭት የሚገባበት ሁኔታ እንዲመቻች አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪና የጣቢያው ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን በበኩላቸው፣ ለጣቢያው የአደረጃጀት ሥራ አስፈላጊው ድጋፍ መደረጉን ገልጸው፣ ቀሪ የቁሳቁስ ግብዓቶችም በአፋጣኝ ተሟልተው ጣቢያው ወደ ስርጭት እንዲገባ ይደረጋል ብለዋል።
በጉብኝቱ ላይ ከኃላፊዎቹ በተጨማሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና ሌሎች የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ምንጭ፦ ቤንች ሸኮ ቴሌቪዥን
