
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት መልስ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦
የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለማሳብ የነበረውን ማነቆ ለመፍታት የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ተጀምሯል።
ወደ አፍሪካ የሚፈሰው እርዳታ በ7 በመቶ ቀንሷል። የዓለም የንግድ ሥርዓትም በከፍተኛ ደረጃ ተጎድቷል።
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃና በሀገሯ ሰፋፊ ፈተናዎች ያሉባት ቢሆንም በባለፈው ዓመት የ8 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት አረጋግጣለች።
በዚህ ዓመት የ8 ነጥብ 4 በመቶ ዕድገት ለማምጣት ታቅዶ ሲሰራ ቆይቷል።
ዘንድሮ 23 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን ከሴፍቲኔት ተረጂነት ነጻ ወጥተዋል ይህ የማንሰራራት ትልቁ ማሳያ ነው፤
በኢትዮጵያ የተጀመረው መስታወት ለማምረት የሚያስችለው ፋብሪካ በቀጣይ ወራት ይጠናቀቃል፤
