



የቦንጋ ማዕከል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ተቋማት የአስተዳደራዊ ዘርፍ የብልጽግና ህብረት አባላት በብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የተቀመጡ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ ተወያዩ።
ውይይቱ ”ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል ፓርቲው በ2ኛ መደበኛ ጉባኤ ያስቀመጡ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ የብልጽግና ቤተሰብ አባላት በተሟላ መንገድ ግንዛቤ በመያዝ ለተፈጻሚነቱ ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ነው።
ፓርቲው በጉባኤው ለቀጣይ ሶስት ዓመታት ለማከናወን ያቀዳቸው ግቦች ለአባላት ቀርበው ውይይት ተደርጓል።
የብልጽግና ህብረት አባላት በበኩላቸው፤ ፓርቲው በቀጣይ ጊዜያት ለማከናወን ያስቀመጣቸው እቅዶች የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠል አጋዥ ጉዳዮች በመሆናቸው ለተፈጻሚነቱ የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት ዝግጁ እንደሆናቸውም ገልጸዋል።
ለጠንካራ ፓርቲና ጠንካራ ሀገር መንግስት ግንባታ የፓርቲውን እሳቤ በአግባቡ የተረዳና ጥራት ያለው አባላት ማፍራት እንዲያስችል የአባላት አቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ በትኩረት እንዲሰራ ጠቁመዋል።
ፓርቲው አካታች ማህበራዊ ልማት መረጋገጥ፣ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ፣ውጤታማ ተቋማትና የሲቪል ሰርቫንት ግንባታ፣ የተጀመሩ አዳዲስ የልማት ኢንሼቲቮችን በማጠናከር የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንሚገባና ፓርቲው ከአባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት መስራት እንደሚጠበቅ ነው አባላት ያነሱት።
ሁሉም የብልጽግና ቤተሰብ አባላት የማህበራዊ ሚዲያ ሠራዊት አባል በመሆን ተሳትፎአቸውን በማሳደግ በፓርቲው ህልውና ላይ የሚነሱ አሉባልታዎችን በተደራጀ መልኩ መመካት እንዳለበትም ተጠይቋል።
የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የቦንጋ ማዕከል የአስተዳደራዊ ዘርፍ የብልጽግና ህብረት ሰብሳቢ አቶ ሳምሶን መለሰ እንደገለጹት፤ ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመፍጠር ብቃትና ጥራት ያለው አመራርና አባላት ማደራጀት፣ የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት መፍጠር ላይ በትኩረት ይሰራል።
ፓርቲው ቀጣይ ለመሥራት ያቀዳቸው ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ተፈጻሚ እንዲሆኑ አባላት በተሰማራበት የስራ መስክ ውጤታማ ተግባራትን መፈጸም እንደሚጠበቅባቸውም አቶ ሳምሶን መለሰ አሳስበዋል።
ፓርቲው ሁሉዓቀፍ የሆነ ማህበረሰብ ተሳትፎ በማጠናከር በሁሉም ዘርፍ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
በፍቅር ከበደ
