




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ክልል ዓቀፍ የመልካም አስተዳደር እና ቅሬታ አቤቱታ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ነዉ
በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና መስተዳድር ምክር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተረፈ ዘዉዴ፤ ከማህበረሰቡ በየደረጃው የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፈታት ህዝቡን ለልማት ከማነሳሳት ባለፈ ህዝቡን ከመንግሥት ጋር በማቀራረብ መልካም ሥራዎች እንዲከናወኑ ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
የመልካም አስተዳደር ችግር በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚ እና በአገልግሎት አሰጣጥ ኢ- ፍትሃዊነት እና አድሎአዊ አሰራር ሲኖር እንደሚከሰትም አቶ ተረፈ ዘዉዴ ተናግረዋል።
የመልካም አስተዳደር ችግር ለቅሬታ ምንጭ ዋነኛ መንስኤ በመሆን ህዝቡን ወደ አልተፈለገ አለመግባባት በመምራት ልማቶች በአንድነት እንዳይፈጽሙ አደጋች እንደሚሆንም ጠቁመዋል።
በክልሉ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን ተቋማዊ በሆነ መልኩ ለመፍታት ከክልል እስከታችኛው መዋቅር ድረስ የመልካም አስተዳደር የጋራ ፎረም ተቋቁሞ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት አቶ ተረፈ ዘዉዴ።
ተቋማት የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን የተቋማችው የዕቅድ አካል አድርገው እንዲፈጸሙ እየተደረገ መሆኑን በመግለፅ የመልካም አስተዳደር ችግር እንዳይከሰት ተግባራትን በአሰራርና በመመሪያ መሠረት ማከናወን እንደሚጠበቅባቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል።
በመድረኩም በምክትል ቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የቅሬታ አበቱታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮናስ ኬና በቅሬታ አቤቱታ ጉዳዮች የተዘጋጀ ሰነድ እያቀረቡ ይገኛሉ።
በፍቅር ከበደ
