7ኛ ጠቅላላ ምርጫየተሳካ እንዲሆን ለማካሄድ አመራሩ በላቀ ትጋትና ቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ

Spread the love

የሸካ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የምርጫ አፈፃፀምና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ የውይይትና የምክክር መድረክ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ አካሂዷል ።

በመድረኩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ እንደሻው እንደተናገሩት በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ፓርቲው በበላይነት እንድያጠናቅቅ አደረጃጀቶችን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል ።

የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ እንደተናገሩት ፓርቲው እስከታችኛው መዋቅር ያለውን ትስስሮችን በማጠናከር ምርጫው ሠላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንድጠናቀቀ አመራሩ የድርሻውን መወጣት አለበት ብለዋል።

ምርጫው ፀጥታውና ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መስራት እንደምገባ ጠቁመው የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማጠናቀቀ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የሸካ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ አለሙ በበኩላቸው ሀገራዊና ክልላዊ ድሎችን በማስቀጠል የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ማጠናቀቅ ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ምርጫውን ነፃ፣ፍታዊና ድሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ብልፅግና ፓርቲ በበላይነት እንድያሸንፍ ሁሉም አመራሮች በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ያስፈልጋል ያሉት አቶ አለማየሁ የአንድነትና ትብብር ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶ ህብረተሰቡ እንድመርጥም የተጀማመሩ የቅስቀሳ ስራዎች መጠናከር እንደሚገባቸው አንስተዋል ።

ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በመቀራረብና የዲሞክራሲ ምህዳሩን በማስፋት ሰላማዊ ፉክክር ለማካሄድ እየተደረጉ ያሉ ስራዎች በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ በጋራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ሁሉንም ማህበራዊ መሠረት ያማከለ የምርጫ ቅስቀሳ በየመዋቅሩ እየተደረገ ያለው መርሃግብር አበረታች መሆኑን ገልፀው በዝህም ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ግልፀኝነት የመፍጠር ስራ ተከናውኗል ብለዋል።

አመራሩና አባላቱ የምርጫ ቦርድን ህግና የፓርቲውን ስነ ምግባር በመከተል የምርጫ ስራዎችን ማከናወን እንደምገባም አሳስበዋል ።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከለውጡ ወዲህ በርካታ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ ያገኘበት፣የተጀመሩ መሠረተ ልማቶችና የኢኒሼቲቭ ስራዎች የምጠናቀቅበት አንዲሁም ምርጫው ፀጥታውና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል ሲል የሸካ ዞን ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *