“7ተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ፣ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒ እንዲሆን በርካታ ሥራዎች እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ ።

Spread the love

በምዕራብ ኦሞ ዞን 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሠላማዊና ስኬታማ እንዲሆን ላይ ዉይይት እና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ በክልሉ በምክትል የርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማድ ክላስተር አስተባባሪ እና የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ እንደተናገረው የዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ የተሳካ እንዲሆን በርካታ ሥራዎች እየተሰራ መሆኑ ተናግሯል ።

ጀግኖች አባቶች ሉዓላዊነቷ ሳይደፈር አስጠብቆ ያቆዩትን ሀገር ይህ ትውልድ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ጠቁመው ፥የሀገር ቀጣይነት የሚወሰነው በዜጎች በሚመሰረተው መንግስት ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

ለዚህም ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ፣ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒ እንዲሆን እየተሰራ ያለዉ ሥራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ቦኒ በበኩላቸው በባለፉት ጊዜያት መንግሥት የሰራቸው ኢንሼቲቦችን አጉልተን በማሳየት ዉጤታማ ምርጫ መካሄድ እንደሚገባ ገልፀዋል ።

የህዝብ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ተናግሯል ።

7ተኛ ሀገራዊ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ ፣ፍትሃዊና ሰላማዊ እንዲሆን የወጣቶች ሴቶች ያለቸዉ ሚና ከፍተኛ በመሆኑን ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ እንዲሆን ከወትሮው ሁሉም በባለቤትነት መሰራት እንደሚገባ ተናግሯል ።

እጩዎች በተገቢው መንገድ ለህዝቡ ማስተዋወቅ ላይ በየደረጃው ያሉት አመራሮች በትኩረት መስራት እንዳለባቸውም አክሎበታል።

በመድረኩ የክልሉ ከፍተኛ የዞን የወረዳ እና የከተማ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *