አዲሱ ስርዓተ ትምህርት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ሚናው የጎላ መሆኑ ተገለፀ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ የአዲሱን ስርዓተ ትምህርት የትውውቅና ስልጠና መድረክ በታርጫ ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የዳውሮ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፍ አቶ ታደለ ታዮ በሀገራችን ያጋጠመውን የትምህርት ስብራት ለመጠገን አሁን ሰፍ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አንስተዋል ።

ትምህርት ቤቶችን ለመማሪ ማስተማ ስራ ምቹ እንዲሆን የማዘጋጀት እና የትምህርት ፖሊስ ማሻሻያ ስራዎች መሰራታቸውንም አንስተዋል ።

የመወያያ ሰነድ ለተሳታፍዎቹ ያቀረቡት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊና ስርዓተ ትምህርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ደረሰ ጋትሳ ሀገራችን ያጋጠመውን የትምህርት ስብራት ለመጠገን የአዲሱ ስርዓተ ትምህር ሁነኛ መፍትሔ እንደሆነም ገልጸዋል ።

በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት በዕውቀት የተካኑ ፣ከቴክኖሎጂ ጋር ቅርብ ትስስር ያላቸው ፣መሰረታዊ ችሎታ ያዳበሩና የተማሩትን በተግባር የሚፈጽሙ ተማሪዎችን ለማፍራት እንደሚገባም ተለሳታፈዎቹ አስገንዝበዋል።

የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ከውይይት በቂ ግንዛቤ መጨበጥ መቻላቸውን አንስተው የመማሪ ማስተማር ስራ ለማቀላጠፍ አስፈላጊ የሆነ የትምህርት ቁሳቁሶችን በተገቢው ማሟላት ይገባል መባሉን የዘገበው ደሬቴድ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *