የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስርዓት ግንባታ ላይ የባለድርሻ አካላት ሚና እንዲጠናከር ተጠየቀ።

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ዘርፍ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ከተለያዩ ሴክተሮች ጋር ያለዉ ግንኙነትና ፋይዳ ዙሪያ ምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካህዷል።

የክልሉ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ዘርፍ ከተለያዩ የመንግሥትና ኃይማኖት ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት የሚያስችለዉን የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሰነድ በማዘጋጀት ተፈራርሞ ወደ ስራ መግባቱ ተገልጿል።

በመድረኩ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስርዓት ግንባታ ከሌሎች ሴክተሮች ጋር ያለዉ ትስስርና የባለድርሻ አካላት ሚና ላይ ገለጻ ተደርጓል።

በዞኖች እየተከናወነ ያለውን የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስረዓት ዙሪያ በተደረገው የድጋፋዊ ክትትል ሪፓርት በዞኖች የተሻለ የመረጃ ስርዐት ቢኖርም በተፈለገው ጊዜ ተገቢውን አግልግሎት ከመስጠት አንጻር ክፍተት እንዳለ ተነገሯል።

የባለድርሻዎች ቅንጅትን መጠናከር ለወሳኝ ኩነት ምዝገባ አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ የወሰኝ ኩነት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ መኩሪያ የወሳኝ ኩነት መረጃ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ በትኩረት መሰራት አለበት ብለዋል።

የሚሰበሰበው መረጃ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍልን ለማረጋገጥ የሚውል በመሆኑ ዜጎች በወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ እንደሚሰራም ኃላፊው አክለዋል።

በክልሉ በተመረጡ 19 የጤና ተቋማት ባለሙያዎችን በጊዜያዊነት በማሰማራት የውልደትና የልደት ምዝገባን ለማካሄድ የሙከራ ስራ መጀመሩ ተገልጿል።

የወሳኝ ኩነት ምዝገባን በቀበሌ ደረጃ በዘመናዊ የመረጃ መመዝቢያ ታብሌትና በክብር መዝገብ የመመዝገብ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ነው የተነገረው።

በወሳኝ ኩነት ዙሪያ የማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ያሳሰቡት የመድረኩ ተሳታፊዎች ማህበራዊ አግልግሎት ሰጪ ተቋማት የወሳኝ ኩነት መረጃ የመጠየቅ ባህልን መዳበር እንዳለበት አንስተዋል።

በመድረኩ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት አቶ ቆጭቶ ገ/ማሪያምን ጨምሮ ሌሎች የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን የትምህርት ፣የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ እና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከወሳኝ ኩነት ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *