የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ለቢስት ባር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ጌታቸው ኬኒ፣ የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ “ቢስት ባር” በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አፈ ጉባኤው በመልዕክታቸው የጠቀሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

“ቢስት ባር” የሕዝብን አብሮነት፣ ሰላም፣ ወዳጅነትና ወንድማማችነትን የሚያደምቅ ትልቅ እሴት መሆኑን ገልጸዋል።

በዓሉ አሮጌውን ዓመት በመሸኘትና አዲሱን ዓመት በመቀበል፣ ሕዝቡ ለአዝመራ እርሻ የሚዘጋጅበትና የእርስ በርስ ግንኙነቱን የሚያጠናክርበት ወቅት መሆኑን ጠቁመዋል።

በዓሉ መከበር ስላለበት ብቻ ሳይሆን፣ አባቶቻችን ለዘመናት ጠብቀው ያቆዩትን መልካም እሴት ለቀጣዩ ትውልድ ለማሸጋገር ትልቅ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

በዓሉ የሕዝቦች አንድነትን በማጠናከር ለሀገር ግንባታ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል።

በመጨረሻም፣ የተከበሩ አቶ ጌታቸው ኬኒ “ቢስት ባር” የመቻቻል፣ የፍቅርና የወንድማማችነት በዓል እንዲሆንላቸው ለቤንች ብሔር ተወላጆችና ለክልሉ ሕዝቦች መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ሲል የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *