በየብሄረሰቡ የሚከበሩ በዓላት “የመደመር ዕሳቤን” ከማጠናከረም ባለፈ ጤናማ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ያጠናክራሉ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ገለጹ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ – ጉባኤ ለቤንች ብሄር ዘመን መለወጫ “ቢስት ባር” የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በክልሉ የአንድ ብሄር ዘመን መለወጫ በዓል ሲከበር የአንዱ ብሄረሰብ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ተባባሪ በመሆን የሚከናወነው ተግባራት ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ – ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩረታ ተናግረዋል።

በየአከባቢው የብሄር ዘመን መለወጫ ለማክበር እየተደረገ ያለው ተሳትፎ “የመደመር ዕሳቤን” ከማጠናከረም ባለፈ ጤናማ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ያጠናክራል ብለዋል ዋና አፈ- ጉባኤው።

በክልሉ በረካታ ብሄር ብሄረሰቦች የዘመን መለወጫ በዓላቸውን እያከበሩ እንደሚገኙት የገለፁት አቶ ወንድሙ ከጥር 4_5/2018 የሚከበረው የቤንች ብሄር ዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቢስት ባር” አንዱና ተጠቃሽ ነው ብለዋል።

ከ”ቢስት ባር ቀጥሎ ጥር 15_16/2018 ዓ.ም የሸኮ ብሄር ዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቲካሻ ቤንጊ” የሚከበር መሆኑን የገለፁት ዋና አፈ- ጉባኤ በተለይም ባህልን ከሀይማኖት እና ባህልን ከፖለቲካ ለይቶ መምራት ከሁሉም የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን ማስገንዘባቸውን የቤንች ሸኮ ቴቪ ዘግቧል።

ዋና አፈ – ጉባኤው የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክርና በድምቀት የሚከበርው የቤንች ብሄር ዘመን መለወጫ “ቢስት ባር”ን አስመልክተው ለመላው የቤንች ብሄረሰቦችና ለአከባቢው ህብረተሰቦች መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *