
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ለቤንች ብሔር የዘመን መለወጫ” ቢስት ባር “በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ አመልዕክት አስተላለፉ
በመልዕክታቸው የጥንት አባቶች የስልጣኔ ማሳያ የሆነው የቤንች ብሔር ዘመን መለወጫ “ቢስት ባር” አዲስ እህል ሲደርስ ቤንቾች ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ተካፍሎ በመቅመስ ከአሮጌው ወደ አዲስ ዓመትን የሚሸጋገሩበትና አዲስ ተስፋን የሚላበሱበት ውብ ባህላዊ እሴት ነው።
በዓሉ ከጨፍጋጋው ክረምት ወደ ጸደይ ብርሃናማ መሸጋገሩን ፣ ቤተሰቡ ፣ ልጆቹ ፣ እርሻው ፣ ከብቶቹና ቀየው በሠላም በመቆየቱ ለፈጣሪ ምስጋና በጋራ የሚያቀርቡበትና የመኸር አዝመራ ደርሶ ፍሬ መስጠት ሲጀምር የበኩር እህል የሚቀመስቀት ስርዓት ነው።
“ቢስት ባር ” በቤንቾች ዘንድ ዘመድ ከአዝማድ መገናኛና መጠያየቂያ፣ የመትረፍረፍ የልምላሜ ፣የፍቅር፣ የተድላና የፍሰሃ በዓል ሲሆን የእርስ-በርስ ግንኙነት የሚያጠናክሩበት፣ የተራራቁ ቤተሰቦችን፣ ወዳጅ ዘመዶችን የሚያቀራርብ ፣ የይቅርታንና የመተባበር መንፈስን የሚያጎለብት ታላቅ ባህላዊ እሴት መሆኑን አንስተዋል።
ቂም፣ጥል፣ ጥላቻና ጥርጣሬ ግድግዳዎችን በመናድ ያለፉትን የታሪክ ምዕራፎችን ዘግቶ በይቅርታና በምህረት ለመሻገር አይተኬ ሚና እንዳለው ገልጸው እነዚህ ባህላዊ ዕሴቶቻችን የወል እውነቶቻችን የብሔራዊነት ትርክቶቻችን መሠረት መሆናቸውንም አንስተዋል።
ቢስት ባር ከባህላዊ እሴትነቱ ባሻገር ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን በማነፅ፣ ዘላቂ ሰላም ባህል ግንባታ፣ እንዲሁም ለሀገረ መንግስት ግንባታ ውጥኖችን ከዳር ለማድረስ አይተኬ ሚና እንዳለው ገልጸው የእሳቶቹ ትረፋት በህዝብ ለህዝብ ትስስርና በሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ የሚመክሩበት፣ ቀጣይ አቅጣጫ የሚቀመጥበት ውብ እሴት መሆኑን ጠቁመዋል።
ህብረተሰቡን ለስራ ለማነሳሳት፣ ወጣቱን በአባቶች ምክር ለማረቅ እና በአንድነት ለሠላም ዘብ ለመቆም፣ ከጎረቤት እና አብሮ ከኖሩ ህብረተሰብ ህብረትን ለመፍጠር፣ ወደ ልማት እና ዕድገት ለመግባት የሚከበር በዓል ነው።
ቢስት ባር የመደመር መርህ ማሳያ ነው ነው ያሉት አቶ ፍቅሬ በአብሮነት፣ ተባብሮ የማደግና ከመበልፀግ እሳቤ ጋር የተሳሰረ ነው ሲሉ አውስተዋል።
የቢስት ባር እሴቶች ከተፈጥሮ ጋር የጣበቀ ቁርኝት ያለው፣ ከግብርና ምርት ጋር የሚተሳሰር እሴት ያለው መሆኑን ጠቅሰው በየአካባቢው ያለን የተፈጥሮ ሀብት ወደ ልማት ለመቀየርና የምግብ ዋስትናን በቤተሰብ ደረጃ ለማረጋገረጋገጥ እንዲሁም ከተረጂነትና ልመና በመላቀቅ የተሟላ ሀገራዊ ሉአላዊነትን በማረጋገጥ ሁለተኛው የአርበኝነት ምእራፍ እውን ለማድረግ ብርቱ ትግል ማድረግ ይጠበቃል ነው ያሉት
ዕሴቶቻችን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍ ብለን የምንታይባቸው የኢኮኖሚ ምንጭና የቱሪዝም መስብ በመሆን የብልጽግናዊ ተምሳሌትነትን የምናረጋግጥባቸው ሌላኛው መንገዳችን ናቸው ያሉት አቶ ፍቅሬ በዚህም የቢስት ባር ዕሴቶቻችን ይዘቱን በጠበቀ መልኩ በማልማት፣ በመንከባከብ ና በማስተዋወቅ ከትውልድ ወደ ትውልድ በማስተላለፍና በዩኔስኮ ቅርስነት ለማስመዝገብ በልዩ ትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።
የቤንች ብሔር በቀደምት አባቶች ለዘመናት አዲስ ዓመትን ሲያከብር የቆየ ቢሆንም ለበርካታ ዓመታት በተለያዩ ምክንያቶች በዓሉ ሳይከበር የቆየ ሲሆን ከለውጡ በኋላ ህብረ- ብሔራዊ አብሮነታችን ማድመቂያ የሆነው የቢስት ባር ደምቆ መታየት ጀምሯል።
“ቢስት ባር” እድለኛ በሆነው የመደመር ትውልድ በመከበሩ የተረሳውን የቤንች ህዝብ ታሪክና ማንነት አካል የሆነው በዓል ዳግም ወደከፍታ ለማድረስ ትልቅ አጋጣሚ ያገኙበትና ታላላቅ የባህል እሴቶቻችንን ለሀገርና ለዓለም ለማስተዋወቅ ምቹ ጊዜ በመፈጠሩ የተሰማቸውን ደሰታ ገልጸዋል።
እነዚህን ድንቅ እሴቶቻችን ለዛሬም ለነገም ስንቅ ነውና ትውልዱ ሊጠብቀው፣ ሊተገብረውና ከትውልድ ወደ ትውልድ ሊያስተላልፈው ይገባልም ብለዋል።
ፓርቲያችን ብዝሃ ባህሎችና እሴቶች
እንዲጎለብቱ፣ ታሪካዊ ቅርሶቻችን የሚዳሰሱም ሆነ የማይዳሰሱ ባህላዊና ትውፊታዊ ቅርሶቻችን ተገቢው ክብርና ትኩረት መስጠቱን ገልፀው ለሀገር ግንባታ
መሣሪያ ሆነው እንዲያገለግሉ እና ለመጪው ትውልድ
እንዲተላለፉ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
ፓርቲያችን ብልጽግና የቀደሙ ባህሎችን ከመጠበቅ ባሻገር ዘመን ተሻጋሪ የትውልድ አሻራና ቅርስ ሆኖ ለመጭው ትውልድ እንዲተላለፉ አበክሮ ይሰራል ብለዋል፡፡
