የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ሴክተር መ/ቤቶች የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ መድረክ በሚዛን አማን ከተማ መካሄድ ጀመረ።

Spread the love

የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ እንዳሉት፣የተቋማትን የመፈፀም አቅም ለማጎልበት እንዲቻል ድጋፍና ክትትል በማደረግ የተጠናከረ የአፈፃፀም ግምገማ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በመድረኩም የተቋማት ስትራቴጂክ ዕቅድ እና ቁልፍ የአፈፃፀም ተግባራትን በመገምገምና በጉዳይ ላይ በልዩ ትኩረት በመወያየት የግምገማው ውጤት ለሚመለከተው አካል የሚቀርብ እንደሆነም ገልፀዋል።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ እና የማክሮ ኢኮኖሚ ዕቅድ ዝግጅት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሚሊዮን አደሞ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው ቢሮው ስራዎችን በዕቅድ በመምራት የተቋማትን አፈጻጸም እና ተነሳሽነት በመለየት ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

መድረኩ በዛሬ ውሎ የኢኮኖሚ ክላስተር የሚገመግም ሲሆን አሁን የግብርና ሴክተር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እየቀረበ ይገኛል።

በካሳሁን አሰፋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *