በክልሉ የተከናወኑ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚብሺን ተከፈተ

Spread the love

በክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተዘጋጀዉ ይህ ኤግዚብሺን በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ።

ፎቶ ኤግዚቢሽኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታና ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በጋራ ከፍተዋል።

የፎቶ ኤግዚቢሽኑ በክልሉ በ2016 ግማሽ ዓመት በክልሉ መንግስት ታቅደው የተከናወኑ የልማት ስራዎች እና የካፒታል ፕሮጀክት አፈጻጸሞችን ያካተተ ነው ።

የፎቶ ኤግዚብሽኑ በክልሉ የተለያዩ ተቋማት የተከናወኑ ተግባራትን ለምክር ቤት አባላትና ለጉባዔዉ ተሳታፊዎች ለማሳወቅ እንደሚረዳ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ና የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ በረከት ኢዮብ አስረድተዋል ።

በኤግዚቢሽኑ የክልሉ ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ፣የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እንዲሁም የክልሉ ምክርቤት አባላትና የጉባኤ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *