በመሠረተ ልማት ዘርፍ በክልሉ አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተናገሩ።

Spread the love

የተከናወኑ ተግባራትን ለምክርቤቱ ያቀረቡት ርዕሰ መስተዳድሩ በመሠረተ ልማት ስራዎች የሚያበረታቱ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል ።

መንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች፤ በሚዛን ዲስትሪክት 56 ኪ.ሜ የመንገድ ግንባታ ለመስራት ታቅዶ 3 ፕሮጀክቶች (25 ኪ/ሜ)፣ በታርጫ ዲስትሪክት 50ኪ.ሜ የመንገድ ግንባታ ሥራ ፕሮጀክቶች ለመስራት ታቅዶ 2 ፕሮጀክቶች (38 ኪ/ሜ) እንዲሁም በቦንጋ ዲስትሪክት ከ (542ኪ.ሜ) የመንገድ ግንባታ ሥራ ፕሮጀክቶች ውስጥ 72 ኪ.ሜ ለመስራት ታቅዶ በ4 ፕሮጀክቶች (52 ኪ/ሜ) የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ስራ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በፈዴራል መንግስት በጀት እየተሰራ ያለዉ የቦንጋ ከተማ ኢመርጀንሲ የመጠጥ ዉሃ ማስፋፊያ ግንባታ ያሉበትን ችግር በመለየት ከወላይታ ሶዶ ዉሃ አገልግሎት ድርጅት በ33,477,228 ብር ዉለታ በመግባት ስራዉን ሙሉ በሙሉ ያጠናቀቁ ሲሆን አሁን ላይ የመስመር ፍተሻ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በባስኬት ፈንድ እየተከናወነ ያለዉ በካፋ ዞን የዋቻ ከተማ ንጹህ መጠጥ ወደ 98% መድረሱን ገልጸዋል፡፡

በዋሽ ፌዝ ሁለት ፕሮጀክት ዳዉሮ ዞን ታርጫ ከተማ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ግንባታ ፕሮጀክት የፊዝካል አፈፃፀም በማጠናቀቅ 24 ሺህ 523 የከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በሸካ ዞን የማሻ ከተማ መጠጥ ዉሃ ግንባታ በቢሮ በኩል ጨረታ ተጠናቆ ለይሁንታ ወደ ዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መላኩንም አብራርተዋል ፡፡

የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሻሻል ባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አብራርተዋል ።

የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሻሻል ባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተናግረዋል ።

የባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎን በማጠናከር በጥሬ ብር ከ251 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ እንደተቻለ ተናግረዋል ።

ከጥሬ ገንዘብ ባሻገርም 6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ መደረጉንና 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት የጉልበት አስተዋጽኦ ለትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማት ማሻሻያ ተድርጓል፡፡

የትምህርት ተደራሽነትን ከማረጋገጥ አኳያ በቅድመ አንደኛ 107 ሺህ 988 ከ1ኛ-12ኛ ክፍል 666 ሺህ 430 ተማሪዎች የመማር ማስተማር ሥራ እየተከናወነ ይገኛልም ብለዋል፡፡

በሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች 32,684፣ በጤና ተቋማት የወሊድ አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል።

በሽታ መከላከልና ቁጥጥር በሚመለከተ በወባ ተጠርጥረው ምርመራ ከተደረገላቸው 437,581 ሰዎች ውስጥ 256,142(58.5%) ሰዎች የወባ በሽታ መኖሩ ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።

አሁን ያለንበት ወቅት የወባ ወረርሽኝ ወቅት መሆኑ ጋር ተያይዞ ከኢትዮጵያ መድሂነት አቅርቦት ኤጀንሲ ጅማና አርባ ምንጭ ቅርንጫፎች በኩል 2,185 ሊትር ባቆረ ውሃ ላይ የሚረጭ ኬሚካል በ52 ወረዳዎች ርጭት እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል፡፡

በተጨማሪ 7,634 ኪ.ግ የጸረ-ወባ ትንኝ ኬሚካል ከፍተኛ ጫና ባለባቸዉ 30 ወረዳዎች ተሰራጭቶ በ601,811 ቤቶች ላይ የቤት ለቤት ርጭት መካሄዱን ገልጸዋል።

ወባ ወረርሸኝን ለመከላከል ክልሉ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ክልላችን የጸጥታ ሥጋት የነበረባቸውን 45 ቀበሌዎችን ከነበሩበት የጸጥታ ሥጋት ወደ ተሻለ አንፃራዊ ሠላም ለማሸጋገር ጠንካራ የቅንጅት ሥራ በ48 ቀበሌዎችን ማሸጋገር ተችሏል ብለዋል።

ከአጎራባች ክልሎች ጋር ያለውን መልካም የመንግስት ለመንግስትና ህዝበ ለህዝብ ግንኙነቶችን ለማጠናከር 2 ጊዜ የጋራ ምክክር መድረኮች መፈጸም መቻሉንም አብራርተዋል ፡፡

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *