የኢትዮጵያን ሕልም አናሰርቅም፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Spread the love

የኢትዮጵያን ሕልም ማንም ሰው ቢያወጣው እና ቢያወርደው እኛ ግን የኢትዮጵያን ሕልም አናሰርቅም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ሕልማችን የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ማድረግ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ ጉዳያችን ግራ ቀኝ አንልም ሲሉ ነው የገለጹት፡፡

በከፍተኛ ኩራት ልንገልጸው የምንፈልገው እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2032 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከፍታ ከአፍሪካ ቢያንስ በ2ኛ ደረጃ የሚቀመጥ ይሆናል ብለዋል፡፡

በ2036 ደግሞ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከአፍሪካ ቀዳሚውን ደረጃ እንደሚይዝ ገልጸው፤ ይህንን እድገት እናሳካለን ማንም ሊያስቆመን አይችልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

ይህን የኢትዮጵያ ሕልም ለማሳካትም በትብብር መሥራት እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *