



ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በአማን ከተማና በሚዛን ከተማ በምዕራፍ ሁለት እየተሰራ ያለውን የኮሪደር ልማት ስራ ምልከታ አድርገዋል።
በጉብኝቱ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማንን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል እንዲሁም የዞንና የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል።
በሚዛን አማን ከተማ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ስራዎች በጥራት ስለመሰራቱ የጥራት ቁጥጥር ኮሚቴዎች ገለጻም አድርገዋል።
ህብረተሰቡ ለልማቱ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ሙሉ ፈቃደኛ ሆነው እየተባበሩ ስለመሆኑም ኮሚቴዎች ተናግረዋል ።
ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የኮሪደር ልማት ስራው በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን በመረዳት በተጀመረው ፍጥነትና ጥራት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል ሲል የቤንች ሸኮ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
