በክልሉ እስካሁን በፀጥታ ዘርፍ የተመዘገቡ ድሎችን በማጽናት ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በትኩረት እየተሰራ ነው፦አቶ አንድነት አሸናፊ

Spread the love

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት በቦንጋ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የክልሉ መንግሥት 2018 በጀት ዓመት የአንደኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ ማጠቃለያውን አግኝቷል።

የመድረኩ ተሳታፊ የነበሩት የክልሉ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ 1ኛ ሩብ ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ እንደመሆኑ መጠን የ2017 ዓ/ም አፈጻጸምን መገምገም፣ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድና ፈጻሚን በብቃት የማዘጋጀት እንዲሁም በየደረጃው ካለው የባለድርሻ አካላት ጋር የማናበብ ስራ በተሳለጠ ሁኔታ መከናወኑን ገልጸዋል።

በሩብ ዓመቱ በአጠቃላይ እንደ አስተዳደር ዘርፍ የሕዝብን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መፍታት እና ተጠቃሚነትኖ ማረጋገጥ የሚያስችሉ ሥራዎች መከናወን መቻሉን የቢሮ ኃላፊው ገልጸዋል።

ከዚህም በመነሳት በፀጥታው ዘርፍ በክልሉ የህግ በላይነትና ሠላምና ፀጥታን የማረጋገጥ ስራ ሲሰራ መቆቱን ያወሱት አቶ አንድነት፤ የፖሊስ መዋቅርን የማጥራት፣ መልሶ የማደራጀት ከክልል እስከታችኛው መዋቅር ሪፎርም የማድረግ ተግባር መከናወኑን አንስተዋል።

በበጀት ዓመቱ በዋናነት እስካሁን በዘርፉ የመጣውን ውጤት ለማላቅ ዘርፌ ብዙ ተግባራት ታቅደው እየተከናወኑ መሆኑን የገለጹት የቢሮ ኃላፊው በአርብቶ አደር አካባቢ ሠላምን በተሟላ መልኩ ለማጽናት በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል።

በከተሞች አካባቢ ዘላቂ ሠላምን ከማስፈን አኳያ የዜጎች ሠላማዊ የእለት ተለት እንቅስቃሴን በማወክ የሚንቀሳቀሱ የሌብነትና ንጥቂያ ወይም መደበኛ ወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን በማንሳት በተሰራው የመከላከል ስራ ውጤት እየታየ መሆኑን ተናግረው፤ ለስኬታማነቱም የማህበረሰብ ደህንነት ፓትሮል፣ የሠላም አደረጃጀቶችንና የተለያዩ ኮሚቴዎችን በየደረጃው የማጠናከርና የማቀናጀት ስራ መሠራቱን አቶ አንድነት ጨምረው ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ከዝግጅት ምዕራፉ ጎን ለጎን የተሰሩ ስራዎች ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ላቅ ያለ ውጤት መመዝገቡን አቶ አንድነት አክሏል።

በመሆኑም የማይቀለበስ አደረጃጀት በመፈጠር በተልዕኮ የሚመራና የህዝብ ባለቤትነት ያረጋገጠ የፀጥታ መዋቅር የመገንባት አስፈላጊ ስራዎች በቀጣይ ጊዜም በትኩረት እንደሚከናወን በአጽንኦት ተናግረዋል።

የመጣውን ሠላም ለማጽናት የሠላሙ ባለቤት የሆነው ህዝብ የሠላም ዋጋውን በመገንዘብ ዘላቂ ሠላምን ለማረጋገጥ ከፀጥታ አካላት ጎን እንዲሰለፍ አሳስበዋል።

በመጨረሻም የቢሮ ኃላፊው የተለያዩ የህዝብ አደረጃጀቶች፣ የሠላም ኮሚቴዎች፣የደህንነት ፓትሮል፣ የህዝብ ምክር ቤቶች እና የሀይማኖት ፎረሞች በክልሉ የተፈጠውን ምቹ መደላደሎች ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ሠላማዊ አካባቢውን በመፍጠር ለክልሉ ህዝብ ልማት ብሎም ለሀገር ሠላም መረጋገጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪውን ጨምረው አስተላልፈዋል ።

በጌታሁን ግርማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *