ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መረቁ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣ በሚዛን አማን ከተማ የተገነባውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በይፋ መርቀው ከፍተዋል።

በአገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ፥ የኢፌዲሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አልማዝ መለሰን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ማዕከሉ ልዩ ልዩ የመንግስት አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል ውስጥ በመስጠት ቀልጣፋ የመንግሥት አግልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ታስቦ በክልሉ መንግስት በጀት የተገነባ መኾኑ ተገልጿል።

ዛሬ ተመርቀው ለአግልግሎት ከፍት የኾነው

ማዕከሉ፥ በመጀመሪያው ምዕራፍ 17 የበቃ የፊት ለፊት የመንግሥት አግልግሎቶችን በመያዝ ወደ ተግባር መግባቱ ነው የተገለጸው።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *