በገቢ አሰባሰብና በታክስ አስተዳደር አዋጆች ህግን በማስከበር ዙሪያ የሚከሰቱ ማነቆዎችን ለመፍታት በትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ትኩረት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

Spread the love

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ጥናት ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ በክልሉ ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 34/2016፣ በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 36/2016 እንዲሁም በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቀጥር 1341/2016 ላይ ለዞን የገቢ ተቋም አመራሮችና ለዘርፉ ባለሙያዎች በቦንጋ ከተማ ሲሰጥ የነበረው የስልጠና መድረክ ተጠናቋል ።

በስልጠናው ማጠቃለያ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ፀደቀ ከፍታው የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊና የታክስ ጥናት ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ የክልሉ ገቢ ተቋም ህግን የማስከበር ስራ እንደሚሰራ በማስታወስ በዘርፉ የወጡ አዋጆችን ለማስፈፀም በትኩረት መሰራት አለበት ብለዋል።

በመሆኑም የዘርፉ ባለሙያዎች አዋጆችን፣ ደንቦችን እና ዝርዝር መመሪያዎችን በአግባቡ በመረዳት ግብር ከፋዩን ማስተማርና ማስገንዘብ በልዩ ሁኔታ መስራት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆን እንደሚገባ አቶ ፀደቀ አጽንኦት ሰጥቷል

በመጨረሻም ክልሉ በአዋጁ ዙሪያ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ በማንሳት ለውጤታማነቱ በየአከባቢው ያሉ የሚድያ አማራጮችን አሟጥጦ መጠቀም ሚናው የጎላ እንደሆነ አንስተዋል።

የክልሉ የገቢ ግብርና የታክስ አስተዳደር አዋጅ ዓላማው ክልሉ ከሚያመነጨው ኢኮኖሚ ግብርና ታክስ በፍትሃዊትና በተገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ እንዲያስችል የሚያግዝ እንደሆነ ስልጠናው ተገልጿል ።

አዲሱ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 በበኩሉ እንደ ሀገር ለተጀመረው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርም ተግባራዊነት ከፍተኛ ሚና በመኖሩ የግብር ከፋዩ ዘንድ ግንዛቤ በመፍጠር ለተግባራዊነቱ ሰልጣኞችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በትኩረት መሥራት እንደሚያስፈልግ በአጽንኦት ተነስቷል ።

ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በክልሉ ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 34/2016፣ በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 36/2016 እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቀጥር 1341/2016 ሰነድ ቀርቦ በተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎርጎበታል።

በውይይቱ ወቅት ግልፀኝነት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ከሰልጣኞች ጥያቄ ተነስተው ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ይህ ስልጠና እስከ ታችኛው መዋቅር እንደሚወርድ ተገልጿል ።

በስልጠና መድረክ ላይ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች እና የሁሉም ዞን ገቢ መምሪያ ኃላፊዎች፣ በገቢዎች መምሪያ የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል ።

በጌታሁን ግርማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *