መንግሥት ነዳጅን ከጎረቤት ሀገራት ባነሰ ዋጋ እያቀረበ መሆኑን የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን አስታወቀ

Spread the love

መንግሥት ነዳጅን ከጎረቤት ሀገራት ባነሰ ዋጋ እያቀረበ መሆኑን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት (ዶ/ር) አስታወቁ።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ደስታው (ዶ/ር) ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋን እየመራ ያለው ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ነው።

ሆኖም መንግሥት በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ በጨመረ ቁጥር ያንን ጭማሪ በአንዴ ወደ ሕዝቡ እያስተላለፈ ዓይደለም ብለዋል።

መንግሥት በነዳጅ ዋጋ ላይ ውሳኔ የሚሰጠው አራት እና አምስት አማራጮችን አጥንቶ መሆኑን በመጥቀስ፤ የዋጋ ጭማሪው በዋጋ ግሽበት ‘ኢንፍሌሽን’ ላይ የሚያመጣውን ተጽዕኖ በብሔራዊ ባንክ እና በማክሮ ኢኮኖሚ ቡድን በኩል ካስገመገመ በኋላ መሆኑን አብራርተዋል።

በዚህም ለሕዝብ ትራንስፖርት የታለመለት ድጎማ በከፍተኛ ሁኔታ ቀጥሏል ያሉት ኃላፊው፤ ለዚሁ ጉዳይ በዚህ ዓመት ብቻ ከመንግሥት ‘ትሬዠሪ’ አራት ቢሊዮን ብር መለቀቁን ተናግረዋል።

ድጎማውን እንደፈለግን ማንሳት አንችልም ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ጉዳዩ ከአጠቃላይ ማክሮ ኢኮኖሚ እና ከሕዝቡ የመግዛት አቅም ጋር የተያያዘ መሆኑን ጠቅሰዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *