





የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በምልከታው ወቅት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ገጽ /ቤት ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ማሞ እንደገለፁት በሚዛን አማን ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ጅምር ስራ አበረታች ደረጃ ላይ በመሆኑን ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።
እንደ ሀገር በሰላሳ ከተሞች የሚተገበረው ይህ የኮሪደር ልማት ውስጥ አንዱ የሚዛን አማን ከተማ መሆኑን ገልፀው ይህንን ለማሳካት በከተማው እየተከናወነ ያለው ተግባር አበረታች መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህ የኮሪደር ልማት እንዲተገበር ማህበረሰቡ በራሱ ተነሳሽነት ቦታ በመልቀቅ እያሳየ ያለው ተግባር የሚደነቅ ነው ያሉት ክቡር አቶ ፀጋዬ ማሞ በቀጣይ የከተማ አስተዳደሩ ነፃ የሆኑ ቦታዎችን በማልማት በአጭር ጊዜ ከተማው ደረጃውን የጠበቀና ከሌሎች ከተሞች ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆን መስራት ይጠበቃልም ነው ያሉት።
የከተማውን ስታንዳርድ ለማስጠበቅ የመንገድ ትራፊክ መጨናነቅ መንስኤ የሚሆነውን የመንገድ ጥበት ለማስፋትና ለእግረኛ መተላለፊያነት እንዲውል በእራስ ተነሳሽነት በማፍረስ ለተባበሩ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
በክልሉ ከተሞችን ውብና ፅዱ፣ ለነዋሪዎች ምቹ ፣ ተመራጭ የቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት መዳራሻ ፣ እንዲሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
መንግስት ለዘርፉ ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት ለሕዝብ ተጠቃሚነት እየሰራ እነደሆነ ገልፀዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በበኩላቸው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የኢኮኖሚ እድገት እና ልማትን ለማምጣት ከፍተኛ ድርሻ ስላለው እንደክልል ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።
ይህን ለማሳካት በክልሉ ባሉ በኮሪደር ልማት በተመረጡ ከተሞች፤የከተሞች ኮሪደር ልማት በአጭር ጊዜ እንዲተገበር እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
በሚዛን አማን ከተማ በፍጥነት እየተከናወነ ያለው ይህ ፕሮጀክት በሌሎች ከተሞች ላይ እንዲሰፋ እንደተሞክሮ ይደረጋል ብለዋል።
በሚዛን አማን ከተማ ህብረተሰቡ ለኮሪደር ልማት እያሳየ ያለውን ተነሳሽነት አድንቀው ይህ ተግባር እንዲሳካ እያደረጉ ያሉ አካላትንም አመስግነዋል።
በሚዛን አማን ከተማ የኮሪደር ልማት ያለበትን ደረጃ የክልል የዞንና የከተማ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ጋር በጋራ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
